Loading
አዝ፦ ዝም ፡ ብዬ (እህህ) ፡ ወደፊት (እህህ) ፡ እገሰግሳለሁ የኋላዬን ፡ ትቼ ፡ የፊቴን ፡ እይዛለሁ (፪x) እይዛለሁ (፪x) ፡ ለጦር ፡ ያስከተተኝ ፡ እርሱን ፡ ደስ ፡ ያሰኘው እይዛለሁ (፪x) ፡ ለጦር ፡ ያስከተተኝ ፡ እርሱን ፡ ደስ ፡ ያሰኘው 1/ለነሰንበላጥ ፡ ለነጊሳም ና ውረድ ፡ ለሚል ፡ ሥራ ፡ ሊያስቆም ከንቱ ፡ ለሆነው ፡ ለዚህ ፡ ቃላቸው አልንበረከክ ፡ ከቶ ፡ አልሰማቸው (፪x) 2/ለሥጋ ፡ ጥቅም ፡ ለነፍሴ ፡ ክሳት እኔ ፡ አልለምንም ፡ በዚህስ ፡ ወራት ለአምላኬ ፡ ደስታ ፡ እሆንለታለሁ ብዙ ፡ ሥራ ፡ ነው ፡ ከፊቴ ፡ ያለው (፪x) አዝማች:> ዝምብዬ (እህህ) ፡ ወደፊት (እህህ) ፡ እገሰግሳለሁ የኋላዬን ፡ ትቼ ፡ የፊቴን ፡ እይዛለሁ (፪x) እይዛለሁ (እይዛለሁ) (፪x) ፡ ለጦር ፡ ያስከተተኝ ፡ እርሱን ፡ ደስ ፡ ያሰኘው እይዛለሁ (እይዛለሁ) (፪x) ፡ ለጦር ፡ ያስከተተኝ ፡ እርሱን ፡ ደስ ፡ ያሰኘው 3/ለይናቅ ፡ ልጆች ፡ ለነፊልሞች በዐይን ፡ ሲታዪ ፡ ለረዣዥሞች ወዬው ፡ እዬዬ ፡ ብዬ ፡ አልጮህም እኔ ፡ የማመልከው ፡ ሽንፈት ፡ አያውቅም (፪x) 4/ድንቃ ፡ ድንቅ ፡ አድርጐ ፡ አንዴ ፡ ጠርቶኛል የእውነትን ፡ መንገድ ፡ አሳይቶኛል: ቀብሬ ልምጣ ብዬ አልጠይቅም ፍሬ ፡ ለሌለው ፡ ጊዜዬን ፡ አልፈጅም (፪x) አዝ፦ ዝም ፡ ብዬ (እህህ) ፡ ወደፊት (እህህ) ፡ እገሰግሳለሁ የኋላዬን ፡ ትቼ ፡ የፊቴን ፡ እይዛለሁ (፪x) እይዛለሁ (እይዛለሁ) (፪x) ፡ ለጦር ፡ ያስከተተኝ ፡ እርሱን ፡ ደስ ፡ ያሰኘው እይዛለሁ (እይዛለሁ) (፪x) ፡ ለጦር ፡ ያስከተተኝ ፡ እርሱን ፡ ደስ ፡ ያሰኘው
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.