Loading
Singer
ዝም አልልም አወራለሁ ታሪኩን ዘም አልልም እናገራለሁ ገድሉን ሞትን ትንሣኤውን ዳግመኛ ምጻቱን (*2) ሰው ጎስቋላ ሆኖ ሃጢያቱ ውጦት የእግዚአብሔር ልጅ ከላይ በሀዘን ተመልክቶት ሊያድነዉ ወደደ ክብሩን ትቶ መቶ ስጋ ለብሶ እንደሰው አሰው ማሕፀን ወቶ ዝም አልልም....(*2) ጊዜው ደረሰና በግርግም ተወልዶ አለምን ሊዋጃት ሆነ ምስኪን ባዶ ሙታንን አስነሳ ለዲዳው አፍ ሰጠው እውርን አበራ ለምፃሙን ዳሰሰው ዝም አልልም....(*2) ሠው ግን አልፈቀደም አዳኙን ሊቀበል ክፋቱ ገፋፋው ሊሰጠው ለመስቀል በርባንም ተፈታ ኢየሱስ በግሩ ገባ ስለ ሰው ሀጥያት የደም እንባ አነባ ዝም አልልም....(*2) መቃብሩ ተናጋ ሳይቆይ በሰልስቱ ከሙታን ተለየ እንደ አምላክነቱ ሄደ ወደ አባቱ አረገ ወደላይ እመጣለሁ ብሎ ሊፈርድ ባለም ላይ ዝም አልልም....(*2)