Loading
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ለስምህ ፡ ዘምራለሁ ፡ ምሥጋናህ ፡ በአፌ ፡ ነው በማለዳ ፡ ምህረትህን ፡ በሌሊትም ፡ እውነትህን ፡ አወራለሁ በእጣ ፡ ክፍሌ ፡ ስለቆምኩ ፡ በፊትህ ፡ ክብርህን ፡ እንዳወራ አጥናለሁ ፡ ሁልጊዜ ፡ የመረጥከኝም ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ ለዚህ ፡ ስራ (፪x) እስካልወሰድክብኝ ፡ እስካለ ፡ እስትንፋሴ ፡ እስካለ ፡ እስትንፋሴ አቀርብልሃለሁ ፡ የነፍሴን ፡ ውዳሴ ፡ የነፍሴን ፡ ውዳሴ (፪x) ክበርብኝ ፡ ክበርብኝ ንገሥብኝ ፡ ንገሥብኝ (፪x) ዓመታቶችህ ፡ አያልቁምና (ዘለዓለማዊ ፡ ዘለዓለማዊ) የዕድሜ ፡ መነሻ ፡ መጨረሻ (ዘለዓለማዊ ፡ ዘለዓለማዊ) የፍጥረት ፡ ንጉሥ ፡ የፍጥረት ፡ ጌታ (ዘለዓለማዊ ፡ ዘለዓለማዊ) ይሰማ ፡ ለአንተ ፡ በኩር ፡ ምሥጋና (ዘለዓለማዊ ፡ ዘለዓለማዊ) (፪x) አንተ ፡ ጥንትም ፡ ነበርክ ፡ ዛሬም ፡ አለህ ለዘላለም ፡ ትኖራለህ ፡ ተከብረህ/ነግሰህ (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.