Loading
ልቤ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ይመኛል የአንተን ፡ ጥሎ ፡ ወዲያ ፡ ይሮጣል አሳልፈህ ፡ አትስጠኝ ፡ ለራሴ በአንተ ፡ ልኑር ፡ አልሁን ፡ በራሴ ልቤ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ይመኛል የአንተን ፡ ጥሎ ፡ በራሱ ፡ ይሮጣል አሳልፈህ ፡ አትስጠኝ ፡ ለራሴ ደርሶ ፡ አሳቢ ፡ ስሆን ፡ ለራሴ እንደ ፡ ልብህ ፡ ልሁን ፡ እንደልብህ እንደ ፡ ሀሳብህ ፡ ልሁን ፡ እንደፈቃድህ (፪x) ፈቃድህ ፡ በልቤ ፡ ላይ ፡ ትሁን ትሰረኝ ፡ በራሴም ፡ አልሁን ቀድመኸኝ ፡ ከወጣህ ፡ ከፊቴ አልፈራም ፡ ብርቱ ፡ ነኝ ፡ አባቴ ጥላህ ፡ ስር ፡ በምቾት ፡ አድራለሁ ዘመኔን ፡ በአንተ ፡ ስር ፡ ከአደረከው (፪x) የተከፈተ ፡ በር ፡ ሁሉ ፡ ከአንተ ፡ አይደለም ነግ ፡ ሊያጐድለኝ ፡ እንጂ ፡ ለመልካም ፡ አይደለም ተደባሎቆ ፡ የገባን ፡ ስኬቴን ፡ አውጣልኝ ፡ ከቤቴ ፡ ከቤቴ ሁሉ ፡ የሞላበት ፡ የሃሰት ፡ ገነት ፡ ምን ፡ ሊበጅ ፡ ያለአንተ ፡ አንተ ፡ የለህበት ይሻለኛል ፡ ያንተው ፡ በረሃ በላይ ፡ እህል ፡ ውኃ (፪x) ዝጋብኝ ፡ የስኬቴን ፡ መንገድ ካልሆነ ፡ ካልመጣ ፡ ከአንተ ፡ ዘንድ የነገን ፡ እዳ ፡ እፈራለሁ ሰግቼ ፡ ለምን ፡ እኖራለሁ ይቅርብኝ ፡ የምቾቴን ፡ መንገድ ካልሆነ ፡ ካልመጣ ፡ ከአንተ ፡ ዘንድ የነገን ፡ ቁጣ ፡ እፈራለሁ ሰግቼ ፡ ለምን ፡ እኖራለሁ እንደ ፡ ልብህ ፡ ልሁን ፡ እንደልብህ እንደ ፡ ሀሳብህ ፡ ልሁን ፡ እንደፈቃድህ (፪x) የአንተን ፡ ውድ ፡ ጊዜ ፡ መጠበቅ ፡ አቅቶኝ የልብህን ፡ ሃሳብ ፡ መታገስ ፡ ተስኖኝ የፈጠንኩ ፡ ሲመስለኝ ፡ ዘግይቼ እንዳልገኝ ፡ ከአየኸው ፡ ወርጄ የእንጀራ ፡ ጩኸቴ ፡ ፡ ጽኑ ፡ ልመናዬ በሞላልኝ ፡ ማግስት ፡ እንዳይሆን ፡ ገዳዬ አንተ ፡ ያልከው ፡ ይሁን ፡ በሕይወቴ እኔ ፡ አልቅደም ፡ ቅደመኝ ፡ አባቴ ዝጋብኝ ፡ የስኬቴን ፡ መንገድ ካልሆነ ፡ ካልመጣ ፡ ከአንተ ፡ ዘንድ የነገን ፡ እዳ ፡ እፈራለሁ ሰግቼ ፡ ለምን ፡ እኖራለሁ ይቅርብኝ ፡ የምቾቴን ፡ መንገድ ካልሆነ ፡ ካልመጣ ፡ ከአንተ ፡ ዘንድ የነገን ፡ ቁጣ ፡ እፈራለሁ ሰግቼ ፡ ለምን ፡ እኖራለሁ (፪x) እንደ ፡ ልብህ ፡ ልሁን ፡ እንደልብህ እንደ ፡ ሀሳብህ ፡ ልሁን ፡ እንደፈቃድህ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.