Loading
Singer
ዛሬማ ፡ ዓይኔ ፡ ያየው ፡ በለጠ ፡ ጆሮዬ ፡ ከሰማው በላዬ ፡ ስለ ፡ ሾምኩህ ፡ ልቤን ፡ ኩራት ፡ አለው (፪x) ንግሥናህን ፡ ሳስበው ፡ ውስጤ ፡ ተደንቀ ፡ መገረም ፡ ተሞላ አንድ ፡ ነህ ፡ ለሕይወቴ ፡ አላውቅም ፡ ከአንተ ፡ ሌላ የለኝም ፡ ከአንተ ፡ ሌላ እንዴት ፡ ያምራል ፡ እንዴት ፡ ውብ ፡ ነው ንጉሥ ፡ ወግህ ፡ ስርዓትህ ፡ ሆ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ያምራል ፡ እንዴት ፡ ውብ ፡ ነው አገዛዝህ ፡ ቅን ፡ ነው ፡ ፍርድህ (፪x) ልዩ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አትጠገብም (፬x) ልዩ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አትጠገብም ልዩ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አልጠገብኩህም (፪x) ማለዳም ፡ ማለዳ ፡ አዲስነትህ ፡ ነው ፡ ልዩ ፡ ያደረገህ ዕድሜውን ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ፈጅቶ የትኛው ፡ ሰው ፡ ለመደህ ፡ የትኛው ፡ ሰው ፡ ጠገበህ ከትላንትናው ፡ ዛሬ ፡ ከዛሬው ፡ ነገ ፡ ይለያል ፡ የክብርህ ፡ ነፀብራቁ ስለዚህ ፡ በልጠህብኛል ፡ ከአልማዝ ፡ ከወርቅ ፡ ከዕንቁ (፪x) ጆሮዬ ፡ ድምጽን ፡ ሰምቶ ፡ አይጠግብም ዓይኔ ፡ ክብርህን ፡ አይቶ ፡ አይጠግብም ምላሴ ፡ ጽድቅህን ፡ አውርቶ ፡ አይጠግብም ቃላቴ ፡ አደናንቆህ ፡ አይጠግብም ልዩ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አትጠገብም (፬x) ልዩ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አትጠገብም ልዩ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አልጠገብኩህም (፪x) እንዴት ፡ ያምራል ፡ እንዴት ፡ ውብ ፡ ነው ንጉሥ ፡ ወግህ ፡ ስርዓትህ ፡ ሆ ኧረ ፡ አንዴት ፡ ያምራል ፡ እንዴት ፡ ውብ ፡ ነው አገዛዝህ ፡ ቅን ፡ ነው ፡ ፍርድህ (፪x) ተወዳዳሪ ፡ አቻ ፡ እና ፡ እኩያ የለህም ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ለዘላለም (፬x)