Loading
Singer
በእርጅና ፡ የወለድኩት ፡ ልጄ ፡ ሞቶብኛል አጥንቱን ፡ ሳያስቀር ፡ አውሬ ፡ በልቶብኛል ወደ ፡ ሙታን ፡ ስፍራ ፡ እያዘንኩ ፡ እወርዳለሁ ስለ ፡ ዮሴፍ ፡ ልጄ ፡ ዝምብዬ ፡ አለቅሳለሁ ከልጆቼ ፡ ሁሉ ፡ ይልቅ ፡ እወደው ፡ ነበር ቀሚስ ፡ ገዝቼለት ፡ ያጌጠች ፡ በህብል አስተዋዩ ፡ ልጄ ፡ ዮሴፍ ፡ ዛሬ ፡ ጠፍቷል ከልብሱ ፡ በስተቀር ፡ ሥጋው ፡ ተቦጫጭቋል እነዛ ፡ ሁለት ፡ ህልሞቹን ፡ ስጠብቅ ፡ ነበር ልጄን ፡ ትልቅ ፡ ቦታ ፡ እንዳየው ፡ ሲከብር ዛሬ ፡ የልጄን ፡ መርዶ ፡ ሰምቼ ፡ አዝኛለሁ ሰዎች ፡ ቢያጽናኑኝስ ፡ እንዴት ፡ አጽናናለሁ ይልጆቼን ፡ ወሬ ፡ አምጣልኝ ፡ ብዬ እኔው ፡ ነኝ ፡ ያዘዝኩት ፡ በበረሃ ፡ ልጄ እራሴው ፡ ነኝ ፡ እኔው ፡ አውሬ ፡ ያስበላሁት የሕይወቱን ፡ ጽዋ ፡ በአንዴ ፡ ያስጨለጥኩት ኧረ ፡ ምነው ፡ ቢቀርብኝ ፡ ባይላክስ ፡ ኖሮ ደህና ፡ አየው ፡ ነበረ ፡ ዮሴፍ ፡ በእድሜው ፡ ከብሮ እናቱም ፡ ወንድሙን ፡ ስታምጥ ፡ ሞታለች ይህንንማ ፡ ብታይ ፡ ምንስ ፡ ትለኛለች እያለ ፡ ሲናገር ፡ ያዕቆብ ፡ በጣም ፡ አዝኖ በልጁ ፡ ዮሴፍ ፡ ሞት ፡ እጅግ ፡ ተጸጽቶ ልጁን ፡ የሚታደግ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለና ዮሴፍ ፡ በሕይወት ፡ አለ ፡ ምስራች ፡ ተሰማ አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ታድጐታልና ዮሴፍ ፡ በሕይወት ፡ አለ ፡ እንደገና (፪x) ሞተ ፡ ብለው ፡ አረዱት ፡ የምስራች ፡ አሉ ቃሉ ፡ ተፈጸመ ፡ ለዮሴፍ ፡ ሰገዱ የዮሴፍ ፡ ወንድሞች ፡ ዮሴፍን ፡ ሸጠዋል ግን ፡ ጌታ ፡ አክብሮት ፡ ሻጩን ፡ ያሰግዳል አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ዮሴፍን ፡ ወዶታል በወንድሞቹ ፡ ላይ ፡ አክብሮታል (፪x) ያዕቆብ ፡ የእንባው ፡ ዘመን ፡ ዛሬ ፡ አበቃለት የዕድሜውም ፡ ፍጻሜ ፡ እልልታ ፡ ሆነለት የሃያ ፡ ብር ፡ ባሪያ ፡ ዛሬ ፡ ጌታ ፡ ሆኗል በምድረ ፡ ግብጽ ፡ ውስጥ ፡ ንጉሥ ፡ አክብሮታል አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ዮሴፍን ፡ ወዶታል በምድር ፡ ሁሉ ፡ ዙሪያ ፡ አክብሮታል እግዚአብሔር ፡ ታድጐታልና ዮሴፍ ፡ በሕይወት ፡ አለ ፡ እንደገና እግዚአብሔር ፡ ታድጐኛልና እኔም ፡ በሕይወት ፡ አለሁ ፡ እንደገና (፪x) እግዚአብሔር ፡ ታድጐሃልና አንተም ፡ በሕይወት ፡ አለህ ፡ እንደገና እግዚአብሔር ፡ ታድጐሻልና አንቺም ፡ በሕይወት ፡ አለሽ ፡ እንደገና እግዚአብሔር ፡ ታድጐናልና እኛም ፡ በሕይወት ፡ አለን ፡ እንደገና(፪x)