Loading
Singer
ዘሩን ፡ ከእምባው ፡ ጋር ፡ የዘራ እርኮ ፡ ተወስዶ ፡ የፈራ ማሲንቆን ፡ አፍሮ ፡ የደበቀ ጠላቱ ፡ ወድቆ ፡ ደቀቀ ቡቃያ ፡ ደርሶ ፡ አፈራ ወይኑ ፡ ዘለላው ፡ ጐመራ በደስታ ፡ ነዶውን ፡ አጨደ ማሲንቆውን ፡ አወረደ አዝ፦ የጉብኝቴ ፡ ዘመን ፡ ፈጠነ የዜማ ፡ ጊዜ ፡ እየደረሰ ፡ እንባዬ ፡ ታበሰ ምርኮዬን ፡ መለሰ ፡ የልቤ ፡ ደረሰ ድል ፡ አስታጠቀኝ ፡ አሄ ፡ ጠላት ፡ አፈረ (፪x) ዳርቻዬን ፡ አሰፋልኝ ፡ ካዝማዬንም ፡ አጸናልኝ ይሄው ፡ ቆመዋል ፡ አግሮቼ ፡ ምርኩዝ ፡ ሆኖልኝ ፡ አባቴ ተሰብሯል ፡ የሃፍረት ፡ ቀንበሬ ፡ ሞልቶታል ፡ አፌን ፡ ዝማሬ ሞገስ ፡ በረከት ፡ ከደጅ ፡ ገብቷል ፡ ኢየሱስ ፡ ወዳጄ አዝ፦ የጉብኝቴ ፡ ዘመን ፡ ፈጠነ የዜማ ፡ ጊዜ ፡ እየደረሰ ፡ እንባዬ ፡ ታበሰ ምርኮዬን ፡ መለሰ ፡ የልቤ ፡ ደረሰ ድል ፡ አስታጠቀኝ ፡ እሰይ/አሜን ፡ ጠላት ፡ አፈረ (፪x) ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ ደስ ፡ ይበልሽ ለምሥጋና ፡ ደግሞ ፡ ተነሽ አጥንቶቼ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ባርኩ ታላቅ ፡ ስሙን ፡ በሉ ፡ አወድሱ አካላቶቼ ፡ በድል ፡ ዘምሩ በነጋ ፡ ጠባ ፡ ስራውን ፡ አብስሩ ያላሳፈረኝ ፡ ሞገስ ፡ የሆነኝ ጌታ ፡ ነውና ፡ ዛሬም ፡ ያገዘኝ በምሥጋና (፫x) ፡ ልቤ ፡ ተነሳ በምሥጋና (፫x) ፡ መጣሁ ፡ እንደገና በምሥጋና (፫x) ፡ ድል ፡ አለ ፡ ገና ልቤ ፡ በሃሴት ፡ በደስታ ፈሰሰ ፡ ቀኔ ፡ ዕልልታ ከአለት ፡ እቃቃት ፡ ወጥቼ ድምጼን ፡ ላሰማ ፡ ለአምላኬ ጭጋጉ ፡ ይሄው ፡ ገፈፈ ሀዘን ፡ ትካዜው ፡ አለፈ ላሞግሰው ፡ እንደገና በድል፡ ዝማሬ ፡ ምሥጋና አዝ፦ የጉብኝቴ ፡ ዘመን ፡ ፈጠነ የዜማ ፡ ጊዜ ፡ እየደረሰ ፡ እንባዬ ፡ ታበሰ ምርኮዬን ፡ መለሰ ፡ የልቤ ፡ ደረሰ ድል ፡ አስታጠቀኝ ፡ እሰይ/አሜን ፡ ጠላት ፡ አፈረ (፪x) ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ ደስ ፡ ይበልሽ ለምሥጋና ፡ ደግሞ ፡ ተነሽ አጥንቶቼ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ባርኩ ታላቅ ፡ ስሙን ፡ በሉ ፡ አወድሱ አካላቶቼ ፡ በድል ፡ ዘምሩ በነጋ ፡ ጠባ ፡ ስራውን ፡ አብስሩ ያላሳፈረኝ ፡ ሞገስ ፡ የሆነኝ ጌታ ፡ ነውና ፡ ዛሬም ፡ ያገዘኝ በምሥጋና (፫x) ፡ ልቤ ፡ ተነሳ በምሥጋና (፫x) ፡ መጣሁ ፡ እንደገና በምሥጋና (፫x) ፡ ድል ፡ አለ ፡ ገና በምሥጋና (፫x) ፡ ልቤ ፡ ተነሳ በምሥጋንና (፫x) ፡ መጣሁ ፡ እንደገና በምሥጋና (፫x) ፡ ድል ፡ አለ ፡ ገና