Loading
Singer
አዝ፦ የዝማሬው ፡ ጉልበት ፡ ያለው ፡ በአፌ ፡ ላይ (፪x) ለአምላኬ ፡ የክብሩ ፡ ሙዳይ ለጠላቴ ፡ የበረዶ ፡ ድንጋይ ለእግዚአብሔር ፡ የክብሩ ፡ ሙዳይ ለጠላቴ ፡ የበረዶ ፡ ድንጋይ የዝማሬው ፡ ቅባት ፡ ያለው ፡ በእኔ ፡ ላይ (፪x) ለአምላኬ ፡ የክብሩ ፡ ሙዳይ ለጠላቴ ፡ የበረዶ ፡ ድንጋይ ለእግዚአብሔር ፡ የክብሩ ፡ ሙዳይ ለጠላቴ ፡ የበረዶ ፡ ድንጋይ ሰልፉን ፡ አይቼ ፡ ልቤ ፡ ሲርድ በእጃቸው ፡ ገባሁ ፡ ዛሬ ፡ ሳልወድ ብዬ ፡ አምላኬን ፡ ምነው ፡ ስል ትዕዛዝ ፡ አወጣ ፡ እንዲህ ፡ ሲል፦ ማለዳ ፡ ቆሜ ፡ ተራራ ፡ ላይ ክብሬን ፡ ዘምሪ ፡ ክብር ፡ እንድታዪ እኔም ፡ ሰምቼው ፡ ስዘምር ሰደደባቸው ፡ ድብቅ ፡ ጦር ማልጄ ፡ ሆ ፡ ብዬ ፡ እነሳለሁ ፡ ከበሮዬን ፡ አነሳለሁ ለአምላኬ ፡ ስዘምርለት ፡ ይርዳል ፡ የጠላቴ ፡ ጉልበት ማልጄ ፡ ሆ ፡ ብዬ ፡ እነሳለሁ ፡ በገናዬን ፡ አነሳለሁ ለአምላኬ ፡ ስዘምርለት ፡ ይፈታ ፡ የጠላቴ ፡ ጉልበት አዝ፦ የዝማሬው ፡ ጉልበት ፡ ያለው ፡ በአፌ ፡ ላይ (፪x) ለአምላኬ ፡ የክብሩ ፡ ሙዳይ ለጠላቴ ፡ የበረዶ ፡ ድንጋይ ለእግዚአብሔር ፡ የክብሩ ፡ ሙዳይ ለጠላቴ ፡ የበረዶ ፡ ድንጋይ የዝማሬው ፡ ቅባት ፡ ያለው ፡ በእኔ ፡ ላይ (፪x) ለአምላኬ ፡ የክብሩ ፡ ሙዳይ ለጠላቴ ፡ የበረዶ ፡ ድንጋይ ለእግዚአብሔር ፡ የክብሩ ፡ ሙዳይ ለጠላቴ ፡ የበረዶ ፡ ድንጋይ ወደ ፡ ጓዳዬ ፡ እንደለመድኩት ለአምላክ ፡ ስዘምር ፡ እንዳደግኩት ዛሬ ፡ አደባባይ ፡ ወጣሁና ሥሙን ፡ ጠራሁት ፡ እንደገና ብላቴኖችን ፡ የሚወደው እግዚአብሔር ፡ ቀባኝ ፡ አትበሉ ፡ እንዴት ፡ ነው ክፉ ፡ መንፈስ ፡ አይቶኝ ፡ ሲሸሽ ጌታ ፡ ይከብራል ፡ ነግቶ ፡ እስኪመሽ ማልጄ ፡ ሆ ፡ ብዬ ፡ እንነሳለሁ ፡ ከበሮዬን ፡ አነሳለሁ ለአምላኬ ፡ ስዘምርለት ፡ ይርዳል ፡ የጠላቴ ፡ ጉልበት ማልጄ ፡ ሆ ፡ ብዬ ፡ እንነሳለሁ ፡ በገናዬን ፡ አነሳለሁ ለአምላኬ ፡ ስዘምርለት ፡ ይፈታ ፡ የጠላቴ ፡ ጉልበት አዝ፦ የዝማሬው ፡ ጉልበት ፡ ያለው ፡ በአፌ ፡ ላይ (፪x) ለአምላኬ ፡ የክብሩ ፡ ሙዳይ ለጠላቴ ፡ የበረዶ ፡ ድንጋይ ለእግዚአብሔር ፡ የክብሩ ፡ ሙዳይ ለጠላቴ ፡ የበረዶ ፡ ድንጋይ የዝማሬው ፡ ቅባት ፡ ያለው ፡ በእኔ ፡ ላይ (፪x) ለአምላኬ ፡ የክብሩ ፡ ሙዳይ ለጠላቴ ፡ የበረዶ ፡ ድንጋይ ለእግዚአብሔር ፡ የክብሩ ፡ ሞዳይ ለጠላቴ ፡ የበረዶ ፡ ድንጋይ