Loading
Singer
በቀድሞው ፡ ስብስብ ፡ በአዲስ ፡ ኪዳን ፡ ህብረት ምዕመናን ፡ አብረው ፡ በተከማቹበት ንብረቱን ፡ ገንዘቡን ፡ ሁሉን ፡ እያመጣ ማንም ፡ ሳይራቆት ፡ እንጀራም ፡ ሳያጣ በአንድ ፡ ልብ ፡ ጌታን ፡ እያመሰገኑ ይቆርሱ ፡ ነበረ ፡ ያኔ ፡ ምዕመኑ ህብረት ፡ እንድናደርግ ፡ ያስተማረን ፡ ቃሉ እንዲህ ፡ ዓይነት ፡ ነበር ፡ ምዕመን ፡ አስተውሉ ዛሬ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ እያሉ ፡ የሚጠሩት በየጐዳናው ፡ ላይ ፡ አስጊጠው ፡ የሰሩት አናጢ ፡ የዋለበት ፡ ከመሰረት ፡ ከላይ በቁመት ፡ በስፋት ፡ ባሻገር ፡ የሚታይ ለዓይን ፡ ጥጋብ ፡ እንጂ ፡ ሕይወት ፡ የሌለበት ያዘነ ፡ የራበው ፡ ደጅ ፡ የሚቆምበት የነፍሳት ፡ ጥሪ ፡ ስብከቱ ፡ ተረስቶ እቁብ ፡ መሰብሰቢያ ፡ ሰው ፡ ጌታ ፡ ቤት ፡ መጥቶ የአዲስ ፡ ኪዳን ፡ ህብረት ፡ የሃዋሪያቱ በአንድ ፡ ልብ ፡ ሁሉም ፡ የቆረሱበቱ ሁሉም ፡ የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ በልብ ፡ በአንደበቱ በዚህ ፡ ዘመን ፡ ይሁን ፡ አሜን ፡ ይሁን ፡ በሉ ያ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ጸሎት ፡ ለቅዱሳን ፡ ሁሉ ሰንበት ፡ ጠብቆ ፡ እንዲያው ፡ ለወጉ መሰባሰቡ ፡ ደንቡን ፡ ማድረጉ ያለክርስቶስ ፡ ኦና ፡ ነው ፡ ቤቱ ጭፈራው ፡ አጉል ፡ ዝማሬው ፡ ከንቱ የዛሬው ፡ ቤተክርስቲያን ፡ ባለአስር ፡ ሺህ ፡ አባላት የቁጥር ፡ እሽቅድምድም ፡ የአባል ፡ ቅጽ ፡ ሙላት መቶ ፡ የነበረው ፡ በሺህ ፡ እንዲቆጠር ማን ፡ ይበልጥ ፡ በብዛት ፡ ብሎ ፡ መፎካከር ህዝቡ ፡ ተጠራቅሞ ፡ አዳራሽ ፡ ይጠባል ሰው ፡ ሰውን ፡ አያውቀው ፡ ይገባል ፡ ይወጣል የዛሬው ፡ እረኛ ፡ አባላት ፡ ይቆጠራል ለጋስና ፡ ሃብታሙን ፡ ለማግኘት ፡ ይጥራል የሥም ፡ ቤተክርስቲያን ፡ ሞልቷል ፡ በየጓሮው ገብተው ፡ ለሚያዩት ፡ ግን ፡ ውስጡ ፡ ግን ፡ ሌላ ፡ ነው መሪዎች ፡ ተብለው ፡ የሚያስተዳድሩ እንደ ፡ ጳውሎስ ፡ መስራት ፡ ሰንፈው ፡ ያልተማሩ ሰርተው ፡ የማያውቁ ፡ ወንበር ፡ የሚያሞቁ በላብ ፡ የማግኘትን ፡ ሚስጥር ፡ የማያውቁ በስልጣን ፡ በገንዘብ ፡ እርስ ፡ በርስ ፡ ጡጫ እግዚአብሔር ፡ በእነርሱ ፡ የዓለም ፡ ማላገጫ በየእሁዱ ፡ ጉባኤው ፡ ስጡ ፡ ስጡ ፡ ሰፍኖ ከሃብታም ፡ ከደሃው ፡ ብር ፡ ተለምኖ ቀድሞ ፡ ከተሰሩት ፡ አብልጥ ፡ የሚያኮራ ባልሚሊዮን ፡ ብር ፡ አዳራሽ ፡ ሊሰራ የእገሌ ፡ ቤተክርስቴን ፡ እጹብ ፡ ድንቅ ፡ ስራ የሰው ፡ ልጅ ፡ የራሱን ፡ ስሙን ፡ እንዲያስጠራ ባዶ ፡ ሆድ ፡ የመጡ ፡ የራባቸው ፡ ሁሉ ለአዳራሹ ፡ መስሪያ ፡ ስጡ ፡ ይባላሉ በሰንበቱ ፡ ህብረት ፡ ግራ ፡ ቀኝ ፡ ላየ ፡ ሰው አለ ፡ በጌታ ፡ ቤት ፡ ያጣ ፡ የሚቆርሰው ሱሪው ፡ የተጣፈ ፡ መጫሚያው ፡ ያለቀ መቆም ፡ የተሳነው ፡ አቅሙ ፡ የደቀቀ ሞልቷል ፡ ውስጡ ፡ የሚጮህ ፡ በጌታ ፡ ፊት ፡ ወድቆ የእግዚአብሔር ፡ ገንዘብ ፡ ግን ፡ ባንክ ፡ ተጨናንቆ ስስታም ፡ መሪዎች ፡ ያው ፡ ሲስገበገቡ የመንግስት ፡ ሲሳይ ፡ አይቀርም ፡ መሆኑ በእግዚአብሔር ፡ ቤት ፡ በረከት ፡ ይብዛ መብል ፡ ይሁን ፡ ለራበው ፡ በዛ የሳጥኑን ፡ ቁልፍ ፡ የያዛችሁ የጌታን ፡ ገንዘብ ፡ ጉዋዳ ፡ ያሸሻችሁ ሰማይ ፡ ጫፍ ፡ ደርሶዋል ፡ መሰሰታችሁ ለራበው ፡ ለጠማው ፡ በትኑት ፡ አውጡና የእግዚአብሔርን ፡ ገንዘብ ፡ ማካበት ፡ ይቅርና