Loading
Singer
አዝ:- መልካሙን ፡ የአምላኬን ፡ ፊት ፡ በጽኑ ፡ እፈልጋለሁ ማልጄ ፡ በማለዳ ፡ ወደእርሱ ፡ እመጣለሁ መንፈሱን ፡ እየሞላ ፡ ዘይቱን ፡ ይቀባኛል ነፍሱን ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ የሰጠው ፡ ኢየሱስ ፡ ይወደኛል ይወደኛል (፬x) ፡ ይወደኛል ፡ ጌታ ፡ ይወደኛል (፫x) ነፍሱን ፡ የሰጠው ፡ ስለእኔ ፡ የታደገኝ ፡ ከኩነኔ ምህረቱን ፡ ያበዛልኝ ፡ የቆመልኝም ፡ ከጐኔ ነፍሴ ፡ ታምናው ፡ ረክታለች ፡ በጸጋው ፡ ብዛት ፡ ቆማለች ያንን ፡ አስፈሪ ፡ ጨለማ ፡ ከአምላኳ ፡ ጋር ፡ ተሻግራለች ያኔ ፡ በመስቀል ፡ ሲሰቃይ ፡ እንደሚወደኝ ፡ ገብቶኛል ሞት ፡ ቢመጣ ፡ በመከራ ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ይመቸኛል ይመቸኛል (፬x) አዝ:- መልካሙን ፡ የአምላኬን ፡ ፊት ፡ በጽኑ ፡ እፈልጋለሁ ማልጄ ፡ በማለዳ ፡ ወደእርሱ ፡ እመጣለሁ መንፈሱን ፡ እየሞላ ፡ ዘይቱን ፡ ይቀባኛል ነፍሱን ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ የሰጠው ፡ ኢየሱስ ፡ ይወደኛል ይወደኛል (፬x) ፡ ይወደኛል ፡ ጌታ ፡ ይወደኛል (፫x) የፍቅሩ ፡ ጥልቀት ፡ ሲገባኝ ፡ ልቤን ፡ ሰጠሁ ፡ እንዲገዛኝ ይንገሥብኝ ፡ ወድጃለሁ ፡ አምላኬ ፡ ነህ ፡ ብዬዋለሁ ዋላ ፡ ውሃን ፡ እንደምትሻ ፡ እኔም ፡ ዘወትር ፡ እጠማዋለሁ በነፍሴ ፡ ወደማደሪያው ፡ ወደ ፡ ፡ እርሱ ፡ እገሰግሳለሁ የሚለየኝ ፡ ማነው ፡ ከእርሱ ፡ በፍቅሩ ፡ ገመድ ፡ አስሮኛል ሞት ፡ ቢመጣ ፡ በመከራ ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ይመቸኛል ይመቸኛል (፬x) አዝ:- መልካሙን ፡ የአምላኬን ፡ ፊት ፡ በጽኑ ፡ እፈልጋለሁ ማልጄ ፡ በማለዳ ፡ ወደእርሱ ፡ እመጣለሁ መንፈሱን ፡ እየሞላ ፡ ዘይቱን ፡ ይቀባኛል ነፍሱን ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ የሰጠው ፡ ኢየሱስ ፡ ይወደኛል ይወደኛል (፬x) ፡ ይወደኛል ፡ ጌታ ፡ ይወደኛል (፫x)