Loading
Singer
የምትወደው ፡ ልጅህን ፡ ወደ ፡ ተራራ ፡ ውሰደው በእዚያም ፡ ለእኔ ፡ ክብር ፡ መስዋዕት ፡ አድርገህ ፡ ሰዋው ጌታ ፡ እንዲህ ፡ ይለኛል ፡ ብዬ ፡ ከቶ ፡ አልጠበኩም ቢሆንም ፡ ሳስተያየው ፡ ከእርሱ ፡ ፍቅር ፡ አይበልጥም እኔም ፡ ሳላወላውል ፡ ወደዚያ ፡ ስፍራ ፡ ደረስኩኝ ልጄን ፡ ለመሰዋት ፡ መሰዊያውን ፡ ሰራሁኝ እንጨትም ፡ ረበረብኩኝ ፡ ልጄን ፡ ይስሐቅ ፡ አሰርኩኝ በዚያም ፡ አጋደምኩኝ ፡ እጄንም ፡ ዘረጋሁኝ ድምጹ ፡ ከሰማይ ፡ መጣ ፡ ሲል ፡ እጅህን ፡ አትዘርጋ አብርሃም ፡ እንደምትወደኝ ፡ በእውነት ፡ ዛሬ ፡ አየሁኝ የእውነት ፡ በረከትን ፡ እባርክሃለሁኝ ልጅህን ፡ ላልከለከልከኝ ፡ በራሴ ፡ ምላለሁኝ አዝ፦ የዋይታና ፡ የመራራ ፡ ለቅሶ ፡ ድምጼን መጽናናት ፡ ሲያቅተኝ ፡ በፊትህ ፡ ያለቀስኩትን እግዚአብሔር ፡ ከሰማይ ፡ ሆኖ ፡ ተመለከተኝ ድምጹንም ፡ አሰማኝ ፡ እንዲህ ፡ አለኝ ዓይንህን ፡ ከእንባ ፡ ከልክል ፡ ድምጽህንም ፡ ከለቅሶ በጣም ፡ ቶሎ ፡ ታያለህ ፡ እንባህ ፡ ከዓይንህ ፡ ታብሶ ኦሆሆ ፡ ኦሆሆ ፡ ኦሆሆ ፡ ምርኮህም ፡ ተመልሶ ፈርዖን ፡ ሲያሳድደኝ ፡ ዳግም ፡ ባሪያው ፡ ሊያደርገኝ በሰረገላው ፡ ብዛት ፡ በሰልፉ ፡ ሲነሳብኝ ቀይ ፡ ባሕርም ፡ ከፊቴ ፡ ሞልቶ ፡ ተደቅኖብኝ ማለፊያ ፡ መንገድ ፡ ጠፍቶኝ ፡ በፍርሃት ፡ ተሞላሁኝ ጌታ ፡ ግን ፡ ቃሉን ፡ ሰጠኝ ፡ ብርሃኑን ፡ አበራልኝ ባሕሩን ፡ እንድትከፍለው ፡ በትርህን ፡ አንሳ ፡ አለኝ እኔም ፡ ለቃሉ ፡ ታዘዝኩ ፡ በጌታ ፡ ላይ ፡ ተደገፍኩ ባሕሩም ፡ ተከፈለ ፡ ጠላቴም ፡ ሰጥሞ ፡ ቀረ አዝ፦ የዋይታና ፡ የመራራ ፡ ለቅሶ ፡ ድምጼን መጽናናት ፡ ሲያቅተኝ ፡ በፊትህ ፡ ያለቀስኩትን እግዚአብሔር ፡ ከሰማይ ፡ ሆኖ ፡ ተመለከተኝ ድምጹንም ፡ አሰማኝ ፡ እንዲህ ፡ አለኝ ዓይንህን ፡ ከእንባ ፡ ከልክል ፡ ድምጽህንም ፡ ከለቅሶ በጣም ፡ ቶሎ ፡ ታያለህ ፡ እንባህ ፡ ከዓይንህ ፡ ታብሶ ኦሆሆ ፡ ኦሆሆ ፡ ኦሆሆ ፡ ምርኮህም ፡ ተመልሶ ከብዙ ፡ የጠላት ፡ ሴራ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ ያተረፍኩህ እንድታገለግለኝ ፡ ልቤን ፡ በአንተ ፡ ያሳረፍኩኝ ብሎ ፡ እንደታማኝ ፡ ባሪያ ፡ ጌታ ፡ ስለቆጠረኝ ወደ ፡ ነነዌ ፡ እንድሂድ ፡ መለዕክትን ፡ ሰጥቶ ፡ ላከኝ እኔ ፡ ግን ፡ በምትኩ ፡ ተርሴስ ፡ ልሄድ ፡ ፈለኩ ብዙ ፡ ዋጋ ፡ ከፈልኩ ፡ በመርከብ ፡ ተሳፈርኩ እንዳልሰማ ፡ እየሆንኩኝ ፡ በፊትህ ፡ ኮበለልኩኝ ቃሉን ፡ በመተላለፍ ፡ እግዚአብሔርን ፡ በደልኩኝ እርሱ ፡ ግን ፡ መቼ ፡ ተወኝ ፡ አምርሮ ፡ ተከተለኝ ነፋሳትን ፡ አዘዘ ፡ ማዕበሉን ፡ አስነሳብኝ እንዲያውም ፡ ይባስ ፡ ብሎ ፡ ከባሕር ፡ ውስጥ ፡ ተጣልኩኝ ሶስት ፡ ቀንና ፡ ሌሊት ፡ በዓሣ ፡ ሆድ ፡ አደርኩ በመከራዬ ፡ ሳለሁ ፡ ወደእግዚአብሔር ፡ ጮህኩኝ ይልቁንም ፡ በንስሃ ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ ተስማማሁ ጌታዬም ፡ ይቅር ፡ አለኝ ፡ ዳግም ፡ ተጠቀመብኝ ነነዌንና ፡ ጌታን ፡ ለማስታረቅ ፡ በቃሁኝ አዝ፦ የዋይታና ፡ የመራራ ፡ ለቅሶ ፡ ድምጼን መጽናናት ፡ ሲያቅተኝ ፡ በፊትህ ፡ ያለቀስኩትን እግዚአብሔር ፡ ከሰማይ ፡ ሆኖ ፡ ተመለከተኝ ድምጹንም ፡ አሰማኝ ፡ እንዲህ ፡ አለኝ ዓይንህን ፡ ከእንባ ፡ ከልክል ፡ ድምጽህንም ፡ ከለቅሶ በጣም ፡ ቶሎ ፡ ታያለህ ፡ እንባህ ፡ ከዓይንህ ፡ ታብሶ ኦሆሆ ፡ ኦሆሆ ፡ ኦሆሆ ፡ ምርኮህም ፡ ተመልሶ