Loading
Singer
የጸና ፡ ግንብ ፡ የሕይወቴ ፡ ምርኩዝ ፡ ሞገሴ ፡ ነው ፡ ለእኔ በእርሱ ፡ ብርታት ፡ በእርሱ ፡ ፀጋ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ጸንቼ ፡ መቆሜ ተዐምረኛ ፡ የተዐምራት ፡ አምላክ ፡ ድንቅን ፡ የሚሰራ ከጌታዬ ፡ ከኢየሱሴ ፡ በቀር ፡ የለም ፡ እውነተኛ ታሪክ ፡ ተገልብጦ ፡ ጠላቴም ፡ ተመቶ በቆፈረው ፡ ጉድጓድ ፡ እርሱ ፡ ራሱ ፡ ገብቶ ስላየሁ ፡ የጌታዬን ፡ ማዳን ፡ ለእርሱማ ፡ አምልኮ ፡ ያንስበታል ስላየሁ ፡ የኢየሱሴን ፡ ማዳን ፡ ለእርሱማ ፡ አምልኮ ፡ ያንስበታል ለእርሱማ ፡ አምልኮ ፡ ያንስበታል ለእርሱማ ፡ ምሥጋና ፡ ያንስበታል (፪x) የተጣለ ፡ ፈጽሞ ፡ እንዳይጠፋ ፡ በምክሩ ፡ እያሰበ ማክበር ፡ ያውቃል ፡ በፀጋ ፡ ላይ ፡ ፀጋ ፡ እይደራረበ አይቻለሁ ፡ ይሄ ፡ በእኔ ፡ ሆኖ ፡ በሕይወት ፡ ዘመኔ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ከአጠገቤ ፡ ቆሞ ፡ አለሁ ፡ ሲል ፡ ከጐኔ ታሪክ ፡ ተገልብጦ ፡ ጠላቴም ፡ ተመቶ በቆፈረው ፡ ጉድጓድ ፡ እርሱ ፡ ራሱ ፡ ገብቶ ስላየሁ ፡ የጌታዬን ፡ ማዳን ፡ ለእርሱማ ፡ አምልኮ ፡ ያንስበታል ስላየሁ ፡ የኢየሱሴን ፡ ማዳን ፡ ለእርሱማ ፡ አምልኮ ፡ ያንስበታል ለእርሱማ ፡ አምልኮ ፡ ያንስበታል ለእርሱማ ፡ ምሥጋና ፡ ያንስበታል (፪x) የበላይ ፡ ቢሉህ ፡ ቢያሞጋግሱህ አንተን ፡ አይገልጹም ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ ቢሉህ የበላይ ፡ ብልህ ፡ ባሞጋግስህ አንተን ፡ አልገልጽህ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ ብልህ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህና (፬x) ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ገናና (፪x) አይጓደል ፡ አምልኮዬ ፡ ለአንተ ፡ ለጌታዬ (፪x) አይጓደል ፡ ምሥጋናዬ ፡ ለአንተ ፡ ለጌታዬ (፪x) ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህና (፬x) ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ገናና (፪x)