Loading
Singer
አዝ፦ የተወጋ ፡ ጐኑን ፡ እጆቼ ፡ ሲነካ እይኖቼ ፡ በሩልኝ ፡ ሕይወት ፡ አለው ፡ ለካ እንደሞተ ፡ አልቀረም ፡ ኢየሱስ ፡ ተነስቷል ለሞተው ፡ ነገሬ ፡ ሕያው ፡ ነፍስን ፡ ዘርቷል ፩) መቃብር ፡ አትሂዱ ፡ የሱስ ፡ በዚያ ፡ የለም ሕያው ፡ ሆኗል ፡ እሱ ፡ ሕያው ፡ ለዘላለም እጆቹን ፡ ነክቸ ፡ እኔ ፡ ፈውስ ፡ አገኘሁ ስለዚህ ፡ ተነስቷል ፡ ተነስቷል ፡ እላለሁ አዝ፦ የተወጋ ፡ ጐኑን ፡ እጆቼ ፡ ሲነካ እይኖቼ ፡ በሩልኝ ፡ ሕይወት ፡ አለው ፡ ለካ እንደሞተ ፡ አልቀረም ፡ ኢየሱስ ፡ ተነስቷል ለሞተው ፡ ነገሬ ፡ ሕያው ፡ ነፍስን ፡ ዘርቷል ፪) ዐይኖቸ ፡ አይተውታል ፡ ኢየሱስ ፡ ተነስቷል በልብ ፡ ጓዳዬ ፡ በኑሮዬ ፡ ገብቷል አትፍራ ፡ ብሎ ፡ አለኝ ፡ ዳሰኝ ፡ ቅረብና አዎ ፡ ሕያው ፡ ሆኗል ፡ ኢየሱስ ፡ እንደገና አዝ፦ የተወጋ ፡ ጐኑን ፡ እጆቼ ፡ ሲነካ እይኖቼ ፡ በሩልኝ ፡ ሕይወት ፡ አለው ፡ ለካ እንደሞተ ፡ አልቀረም ፡ ኢየሱስ ፡ ተነስቷል ለሞተው ፡ ነገሬ ፡ ሕያው ፡ ነፍስን ፡ ዘርቷል ፫) ዛሬስ ፡ አምሮበታል ፡ ባባቱ ፡ ቀኝ ፡ አለ ሁሉን ፡ በመታዘዝ ፡ ስለተቀበለ ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ስምም ፡ ተሰጥቶታል ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ የሱስ ፡ ጌታ ፡ ነህ ፡ ይሉታል አዝ፦ የተወጋ ፡ ጐኑን ፡ እጆቼ ፡ ሲነካ እይኖቼ ፡ በሩልኝ ፡ ሕይወት ፡ አለው ፡ ለካ እንደሞተ ፡ አልቀረም ፡ ኢየሱስ ፡ ተነስቷል ለሞተው ፡ ነገሬ ፡ ሕያው ፡ ነፍስን ፡ ዘርቷል ፬) ተስፋ ፡ እንደሌለው ፡ እንበታተንም ሰብሳቢ ፡ ቃል ፡ አለው ፡ እኛ ፡ አንወድቅም የሞተ ፡ የማይሰማ ፡ አምላክ ፡ አናመልክም ይሰራል ፡ ተነስቷል ፡ ሕያው ፡ ነው ፡ ዘላለም አዝ፦ የተወጋ ፡ ጐኑን ፡ እጆቼ ፡ ሲነካ እይኖቼ ፡ በሩልኝ ፡ ሕይወት ፡ አለው ፡ ለካ እንደሞተ ፡ አልቀረም ፡ ኢየሱስ ፡ ተነስቷል ለሞተው ፡ ነገሬ ፡ ሕያው ፡ ነፍስን ፡ ዘርቷል