Loading
Singer
ከዘመድ ፡ አዝማድህ ፡ ተለይተህ ፡ ውጣ የሚልን ፡ ድምጽ ፡ ሰምቶ ፡ በእምነት ፡ የወጣ [1] አብርሃም ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ መቶ ፡ ዕድሜ ፡ ሊሞላ አስር ፡ አመት ፡ ቀረው ፡ ሊሻገር ፡ እርጅናን [2] ሲዘገይ ፡ የተስፋው ፡ ቃልኪዳን ፡ ሲጠፋ ከአብርሃምና ፡ ሳራ ፡ ተሟጠጠ ፡ ተስፋ ሃሳባቸውን ፡ ሳቱ ፡ እስማኤልም ፡ መጣ [3] ለዛ ፡ ጻድቅ ፡ ሰው ፡ ቤት ፡ ሁከትን ፡ አመጣ ነገር ፡ ግን ፡ ለመቶ ፡ አንዲት ፡ አመት ፡ ስትቀር የሳራን ፡ ማህጸን ፡ አሰበ ፡ እግዚአብሔር [4] ይስሃቅ ፡ የተስፋው ፡ ልጅ ፡ ወዲያው ፡ ተወለደ የተስፋው ፡ ጨለማ ፡ ተወገደ (፪x) [5] አዝ፦ የተስፋው/የተስፋህ ፡ ቃል ፡ ምንም ፡ ቢዘገይም መፈጸሙ ፡ አይቀርም የተስፋ/የተስፋሽ ፡ ቃል ፡ ቢዘገይም ፡ እንኳን ፍሬ ፡ አለው ፡ በኋላ (፪x) እስራኤላውያን ፡ ከነዓን ፡ እንዳይገቡ ጋሬጣ ፡ ሆነባቸው ፡ የእያሪኮ ፡ ግንቡ ቀንደ ፡ መለከትን ፡ በእጃቸው ፡ ይዘው በታላቅ ፡ ዝማሬ ፡ ሊነድሉት ፡ ቆርጠው ፍፁም ፡ ሳይሰለቹ ፡ ህዝቡና ፡ እያሱ የእያሪኮን ፡ ቅጥር ፡ ሊደረማምሱ ቆርጠው ፡ ተነስተዋል ፡ ዙረት ፡ ጀምረዋል ይኸው ፡ ሳይነደል ፡ ስድስት ፡ ቀን ፡ አልፎታል ግን ፡ ለመጨረሻ ፡ መዞር ፡ ጀምረዋል መለከት ፡ መንፋቱን ፡ ተያይዘውታል በዚህ ፡ ታላቅ ፡ ተስፋ ፡ እያሪኮን ፡ ሲዞሩ የእያሪኮን ፡ ቅጥር ፡ አፈረሱ (፪x) አዝ፦ የተስፋው/የተስፋህ ፡ ቃል ፡ ምንም ፡ ቢዘገይም መፈጸሙ ፡ አይቀርም የተስፋ/የተስፋሽ ፡ ቃል ፡ ቢዘገይም ፡ እንኳን ፍሬ ፡ አለው ፡ በኋላ (፪x) ሃናም ፡ መካኗ ፡ ሴት ፡ ልጅን ፡ ያልወለደች ለብዙ ፡ አመታት ፡ ብዙ ፡ ያለቀሰች ሁልጊዜ ፡ ወደ ፡ አምላኳ ፡ የምታፈስ ፡ እንባ ከአስር ፡ ልጆች ፡ ሁሉ ፡ ያልተሻላት ፡ ባሏ [6] ወደ ፡ ቤተ ፡ መቅደስ ፡ ስትጸልይ ፡ ገብታ እንባዋን ፡ ስትዘራ ፡ ለላይኛው ፡ ጌታ ካህኑ ፡ ኤሊ ፡ ግን ፡ ሰካራም ፡ ነሽ ፡ አላት የልቧል ፡ ሰቆቃ ፡ መቼ ፡ ተረዳላት [7] አምላኬ ፡ ልጅ ፡ ስጠኝ ፡ ለአንተው ፡ ሰጥሃለሁ ይኸው ፡ ተንበርክኬ ፡ ቃልኪዳን ፡ እገባለሁ [8] እያለች ፡ በተስፋ ፡ ስትጠብቅ ፡ ሳትሰለች ሳሙኤልን ፡ . (1) . ፡ ወለደች (፪x) [9] አዝ፦ የተስፋው/የተስፋህ ፡ ቃል ፡ ምንም ፡ ቢዘገይም መፈጸሙ ፡ አይቀርም የተስፋ/የተስፋሽ ፡ ቃል ፡ ቢዘገይም ፡ እንኳን ፍሬ ፡ አለው ፡ በኋላ (፪x) ማርያምና ፡ ማርታ ፡ ታላቅ ፡ ወንድማቸው እጅግ ፡ የሚወዱትም ፡ ያ ፡ መመኪያቸው አልዓዛር ፡ ታሞ ፡ አልጋ ፡ ላይ ፡ ተኝቷል መሞቱም ፡ አይቀርም ፡ ብለውም ፡ ሰግተዋል ቶሎ ፡ በአፋጣኝ ፡ መልዕክትን ፡ ሰደዱ ወዳጁን ፡ ኢየሱስን ፡ ሊያስጠሩ ፡ ወደዱ ግን ፡ የአላዓዛር ፡ ሀመም ፡ እያደረ ፡ ባሰ እዛው ፡ በተኛበት ፡ ወንድማቸው ፡ ሞተ ተስፋቸውን ፡ ቆረጡ ፡ ወስደውም ፡ ቀበሩት አራት ፡ ቀን ፡ አለፈ ፡ ዋሻ ፡ ውስጥ ፡ ጣሉት ግን ፡ በአራተኛው ፡ ቀን ፡ ያ ፡ ወዳጁ ፡ መጣ ሟችሁን ፡ ከሙት ፡ በሃል ፡ አወጣ (፪x) አዝ፦ የተስፋው/የተስፋህ ፡ ቃል ፡ ምንም ፡ ቢዘገይም መፈጸሙ ፡ አይቀርም የተስፋ/የተስፋሽ ፡ ቃል ፡ ቢዘገይም ፡ እንኳን ፍሬ ፡ አለው ፡ በኋላ (፪x)