Loading
Singer
Updated 8/31/2026
አዝ፦ የተሰዋህ ፡ የእግዚአብሔር ፡ በግ የሞትክልኝ ፡ አምላኬ ፡ ሆይ ጭንቀት ፡ ጣርህ ፡ ለነፍሴ ፡ ይታይ (፪x) ሃዘን ፡ ውጦኝ ፡ ሳለሁ ፡ ተጨንቄ በድቅድቅ ፡ ጨለማ ፡ ውስጥ ፡ ወድቄ ሳላስበው ፡ ድንገት ፡ ኢየሱስ ፡ ጠርቶኝ የሕይወትን ፡ ውኃ ፡ አፈሰሰልኝ አዝ፦ የተሰዋህ ፡ የእግዚአብሔር ፡ በግ የሞትክልኝ ፡ አምላኬ ፡ ሆይ ጭንቀት ፡ ጣርህ ፡ ለነፍሴ ፡ ይታይ (፪x) የኀጢአት ፡ ሸክም ፡ እጅግ ፡ ጀብዶብኝ ምንም ፡ አጥቼ ፡ የሚረዳኝ ኢየሱሴ ፡ ድንገት ፡ ደርሶልኝ ከድካሜ ፡ ሁሉ ፡ አሳረፈኝ አዝ፦ የተሰዋህ ፡ የእግዚአብሔር ፡ በግ የሞትክልኝ ፡ አምላኬ ፡ ሆይ ጭንቀት ፡ ጣርህ ፡ ለነፍሴ ፡ ይታይ (፪x) በሰይጣን ፡ ሰንሰለት ፡ ታስሬ ወደገሃነም ፡ እሳት ፡ ሳመራ ኢየሱሴ ፡ ለእኔ ፡ ዋስ ፡ ሆኖ አወጣኝ ፡ ከዚያ ፡ መከራ አዝ፦ የተሰዋህ ፡ የእግዚአብሔር ፡ በግ የሞትክልኝ ፡ አምላኬ ፡ ሆይ ጭንቀት ፡ ጣርህ ፡ ለነፍሴ ፡ ይታይ (፪x) ተስፋ ፡ አልነበረኝም ፡ ከቶ ከሲኦል ፡ ውስጥም ፡ ለመውጣቴ በመስቀል ፡ ለእኔ ፡ ሞቶ ፡ አዳነኝ ያየዋሁ ፡ ቸሩ ፡ አባቴ አዝ፦ የተሰዋህ ፡ የእግዚአብሔር ፡ በግ የሞትክልኝ ፡ አምላኬ ፡ ሆይ ጭንቀት ፡ ጣርህ ፡ ለነፍሴ ፡ ይታይ (፪x)