Loading
Singer
የታሰረችው ፡ ውርንጭላ ፡ ለኢየሱስ ፡ መቀመጫ ታስፈልገዋለችና ፡ አምጧት ፡ በፍጥነት/በቶሎ ፡ ፍቱና (፪x) ለምን ፡ ቢባል ፡ ሊከብርባት ፣ ለምን ፡ ቢባል ፡ ሊነግስባት እራሱን ፡ በላዯ ፡ አድርጐ ፡ ኢየሩሳሌም ፡ ሊገባባት/ሊጓዝባት (፪x) አዝ፦ የተፈታው ፡ እስራቴ ፡ የታወጀው ፡ አርነቴ በቀራንዮ ፡ በጐልጐታ ፡ እራሱን ፡ ሲሰጥ ፡ ለእኔ ፡ ጌታ ተፈጸመ ፡ ሲል ፡ ሲናገር ፡ የተጫነኝ ፡ ክፉ ፡ ቀንበር ሲወድቅ ፡ አየሁ ፡ ሲሰባበር ፡ ይሁን ፡ ለእርሱ ፡ ብዙ ፡ ክብር በድቅድቁ ፡ ጨለማ ፡ ተጥዬ ፡ ስደናበር በጠበቀው ፡ ሰንሰለት ፡ ባማይፈታው ፡ እስር እንድጠፋ ፡ ለሲዖል ፡ የታጨሁ ፡ በመሆኔ በግፍ ፡ ነፍሴ ፡ ሊሰዋ ፡ ሊታረድ ፡ በጭካኔ አዋጅ ፡ ወጣ ፡ ከሰማይ ፡ ከዙፋን ፡ ከመቅደሱ ፍቷትና ፡ ትለቀቅ ፡ ተባለ ፡ ክብር ፡ ለእርሱ አገኛታለሁ ፡ ብሎ ፡ የጐመጀው ፡ ጠላቴ እፍረት ፡ ተከናነበ ፡ እኔም ፡ ጸና ፡ ጉልበቴ አዝ፦ የተፈታው ፡ እስራቴ ፡ የታወጀው ፡ አርነቴ በቀራንዮ ፡ በጐልጐታ ፡ እራሱን ፡ ሲሰጥ ፡ ለእኔ ፡ ጌታ ተፈጸመ ፡ ሲል ፡ ሲናገር ፡ የተጫነኝ ፡ ክፉ ፡ ቀንበር ሲወድቅ ፡ አየሁ ፡ ሲሰባበር ፡ ይሁን ፡ ለእርሱ ፡ ብዙ ፡ ክብር አጥምዶብኝ ፡ ወጥመዱን ፡ እግሮቼ ፡ ስር ፡ ዘርግቶ መረብ ፡ ውስጥ ፡ እንድገባ ፡ ፈልጐ ፡ እጅግ ፡ ጓጉቶ መስሎት ፡ የተሳካለት ፡ የገባሁ ፡ በመዳፉ ደስ ፡ ብሎት ፡ ጨፈረ ፡ ሊውጠኝ ፡ ይዞ ፡ በአፉ የይሁዳው ፡ አንበሳ ፡ የቀራንዮ ፡ ጀግና ጉልበተኛው ፡ ኢየሱስ ፡ ስመጥሩ ፡ ገናና ፍፁም ፡ አይሆንም ፡ ብሎ ፡ ከሰማያት ፡ ወረደ እራሱን ፡ ስለእኔ ፡ ሲሰጥ ፡ ጠላቴ ፡ ተዋረደ አዝ፦ የተፈታው ፡ እስራቴ ፡ የታወጀው ፡ አርነቴ በቀራንዮ ፡ በጐልጐታ ፡ እራሱን ፡ ሲሰጥ ፡ ለእኔ ፡ ጌታ ተፈጸመ ፡ ሲል ፡ ሲናገር ፡ የተጫነኝ ፡ ክፉ ፡ ቀንበር ሲወድቅ ፡ አየሁ ፡ ሲሰባበር ፡ ይሁን ፡ ለእርሱ ፡ ብዙ ፡ ክብር ወገኖች ፡ የምስራች ፡ ተሸንፏል ፡ ዲያቢሎስ የሞትን ፡ ጣር ፡ ባጠፋው ፡ በእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ በኢየሱስ ከመስቀሉ ፡ ስር ፡ ያኔ ፡ አድቅቆታል ፡ ቀጥቅጦ ለሚያምኑበት ፡ በሙሉ ፡ አስገዝቶታል ፡ ረግጦ ወጥመዱ ፡ ተሰበረ ፡ ነፍሴ ፡ እንደወፍ ፡ በረረች ሰይጣን ፡ ባዶ ፡ እጁን ፡ ቀረ ፡ ከግዞቱ ፡ አመለጠች ሞትስ ፡ መውጊያው ፡ የታለ ፡ ጌታ ፡ ሞቶ ፡ ተነሳ ከሲዖል ፡ ምርኮን ፡ ማርኮ ፡ በስልጣኑ ፡ ድል ፡ ነሳ አዝ፦ የተፈታው ፡ እስራቴ ፡ የታወጀው ፡ አርነቴ በቀራንዮ ፡ በጐልጐታ ፡ እራሱን ፡ ሲሰጥ ፡ ለእኔ ፡ ጌታ ተፈጸመ ፡ ሲል ፡ ሲናገር ፡ የተጫነኝ ፡ ክፉ ፡ ቀንበር ሲወድቅ ፡ አየሁ ፡ ሲሰባበር ፡ ይሁን ፡ ለእርሱ ፡ ብዙ ፡ ክብር (፪x)