Loading
Singer
የጠበኩት ፡ ጌታ ፡ ድንገት ፡ ይመጣል (፪x) አሜን ፡ ድንገት ፡ ይመጣል ፡ ሁሉን ፡ ዉብ ፡ ያደርጋል የጠበኩት ፡ ጌታ ፡ ድንገት ፡ ይመጣል (፪x) እሰይ ፡ ድንገት ፡ ይመጣል ፡ ሁሉን ፡ ዉብ ፡ ያደርጋል ዞር ፡ በል ፡ ጠላቴ ፡ አትነዝንዘኝ ፡ ዞር ፡ በልልኝ መቼ ፡ ሊረሳኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ አባት ፡ የሆነኝ ስንቱን ፡ አልፌያለሁ ፡ በእርሱ ፡ ብርታት ፡ በጀርባው ፡ አዝሎኝ አሁንም ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ፈጥኖ ፡ ሊረዳኝ አልተውሽም ፡ ብሎ ፡ ተናግሮኛል እንደሱ ፡ እውነተኛ ፡ የት ፡ ይገኛል (፪x) ያስጨበጠንኝ ፡ ቃል ፡ እየዛለሁ በቃሉ ፡ ይገኛል ፡ አምነዋለሁ በቃሉ ፡ ይገኛል ፡ አምነዋለሁ (፪x) ድንገት ፡ ይመጣል ፡ (ድንገት ፡ ይመጣል) ድንገት ፡ ይመጣል ፡ አሜን ድንገት ፡ ይመጣል ፡ ሁሉን ፡ ይለውጣል (፫x) ድንገት ፡ ሲመጣ ፡ አሃ ፡ አሃሃ ፡ ወደ ፡ መቅደሱ እምባን ፡ በማበስ ፡ አሃ ፡ አሃሃ ፡ ማነው ፡ እንደሱ ሰብሬ ፡ አልፋለሁ ፡ አሃ ፡ አሃሃ ፡ የነሃሱን ፡ ደጃፍ መቆም ፡ አልሻም ፡ ከቶ ፡ ጌታ ፡ ስለሚያልፍ ድንገት ፡ ይመጣል ፡ (ድንገት ፡ ይመጣል) ድንገት ፡ ይመጣል ፡ አሜን ድንገት ፡ ይመጣል ፡ ሁሉን ፡ ይለውጣል ድንገት ፡ ይመጣል ፡ (ድንገት ፡ ይመጣል) ድንገት ፡ ይመጣል ፡ እሰይ ድንገት ፡ ይመጣል ፡ ሁሉን ፡ ይለውጣል እርሱን ፡ ብዬ ፡ የምን ፡ ጭንቀት ፡ እሱን ፡ ብዬ ፡ (እሱን ፡ ብዬ) ያለስጋት ፡ ልቀመጥ ፡ እንጂ ፡ ተዘልዬ (፪x) ቢዘገይም ፡ እኮ ፡ በርግጥ ፡ ይመጣል ፡ (ይመጣል) ሁሉን ፡ ነገሬን ፡ አዲስ ፡ ያደርጋል ፡ (አዲስ ፡ ያደርጋል) በቀጠረው ፡ ሰዓት ፡ በራሱ ፡ ጊዜ ፡ (በራሱ ፡ ጊዜ) በእርሱ ፡ ይገሠጻል ፡ ሃዘን ፡ ትካዜ (፪x) እሱን ፡ ብዬ ፡ የምን ፡ ጭንቀት ፡ እሱን ፡ ብዬ ፡ (እሱን ፡ ብዬ) ያለስጋት ፡ ልቀመጥ ፡ እንጂ ፡ ተዘልዬ (፪x) ቢዘገይም ፡ እኮ ፡ በርግጥ ፡ ይመጣል ፡ (ይመጣል) ሁሉን ፡ ነገሬን ፡ አዲስ ፡ ያደርጋል ፡ (አዲስ ፡ ያደርጋል) በቀጠረው ፡ ሰዓት ፡ በራሱ ፡ ጊዜ (በራሱ ፡ ጊዜ) በእርሱ ፡ ይገሠጻል ፡ ሃዘን ፡ ትካዜ (፪x)