Loading
Singer
አዝ፦ በረከትና ፡ ክብርም ፡ ጥበብም ባለጸግነት ፡ ኃይልም ፡ ብርታትም በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ለተቀመጠው ለነበረው ፡ ላለው ፡ ለሚመለሰው ለታረደው ፡ በግ ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው (፬x) አዝ፦ በረከትና ፡ ክብርም ፡ ጥበብም ባለጸግነት ፡ ኃይልም ፡ ብርታትም በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ለተቀመጠው ለነበረው ፡ ላለው ፡ ለሚመለሰው ለታረደው ፡ በግ ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው (፬x) መጽሐፉን ፡ ትወስድ ፡ ዘንድ ማኅተሞቹንም ፡ ትፈታ ፡ ዘንድ ፡ ይገባሃል ታርደሃልና ፡ በደምህም ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ከነገድ ፡ ሁሉ ከቋንቋም ፡ ሁሉ ፡ ከወገንም ፡ ሁሉ ከሕዝብም ፡ ሁሉ ፡ ሰዎችን ፡ ዋጅተህ ለአምላካችን ፡ መንግሥትና ፡ ካህናት ፡ ይሆኑ ፡ ዘንድ ፡ አደረካቸው በምድርም ፡ ላይ ፡ ይነግሳል ፡ እያሉ አዲስን ፡ ቅኔ ፡ ይዘምራሉ [1] መጽሐፉን ፡ ወስዶ ፡ ማኅተሙን ፡ ፈቶ ከሕዝብም ፡ ሁሉ ፡ ሰዎችን ፡ ዋጅቶ ለአምላክ ፡ መንግሥት ፡ ካህናት ፡ ሆንን በበጉም ፡ ስራ ፡ ተመሰገንን አዝ፦ በረከትና ፡ ክብርም ፡ ጥበብም ባለጸግነት ፡ ኃይልም ፡ ብርታትም በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ለተቀመጠው ለነበረው ፡ ላለው ፡ ለሚመለሰው ለታረደው ፡ በግ ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው (፬x) በሰማይና ፡ በምድርም ፡ ከምድርም ፡ በታች በባሕርም ፡ ላይ ፡ ያለ ፡ ፍጥረት ፡ ሁሉ በእነርሱም ፡ ውስጥ ፡ ያለ ፡ ሁሉ በረከትና ፡ ክብር ፡ ምሥጋናም ኃይልም ፡ ከዘለዓለም ፡ እስከዘለዓለም በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ለተቀመጠው ለበጉም ፡ ይሁን ፡ ሲሉ ፡ ሰማሁ [2] በሰማይ ፡ በምድርም ፡ ከምድርም ፡ በታች በእነርሱም ፡ ውስጥ ፡ ያለን ፡ ፍጥረታት ከዙፋኑ ፡ ፊት ፡ እንወድቃለን ለበጉም ፡ ክብር ፡ እንዘምራለን አዝ፦ በረከትና ፡ ክብርም ፡ ጥበብም ባለጸግነት ፡ ኃይልም ፡ ብርታትም በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ለተቀመጠው ለነበረው ፡ ላለው ፡ ለሚመለሰው ለታረደው ፡ በግ ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው (፬x) አየሁም ፡ በዙፋኑም ፡ በእንስስሶቹም ፡ በሽማግሌዎቹም ፡ ዙሪያ የብዙ ፡ መላእክትን ፡ ድምጽ ፡ ሰማሁ ቁጥራቸውም ፡ አእላፋት ፡ ጊዜ ፡ አእላፋት ፡ እና ፡ ሺ ፡ ጊዜ ፡ ሺ ፡ ነበረ በታላቅም ፡ ድምጽ ፡ የታረደው ፡ በግ ፡ ኃይልና ፡ ባለጠግነት ፡ ጠብብም ፡ ብርታትትም ፡ ክብርም ፡ ምሥጋናም በረከትም ፡ ሊቀበል ፡ ይገባዋል ፡ አሉ [3] እልፍ ፡ አእላፋት ፡ ብዙ ፡ መላእክት ለታረደው ፡ በግ ፡ እሚሰግዱለት እስከዘለዓለም ፡ ለሚኖር ፡ ጌታ ቅኔ ፡ ሲቀኙ ፡ ጥዋትም ፡ ማታ አዝ፦ በረከትና ፡ ክብርም ፡ ጥበብም ባለጸግነት ፡ ኃይልም ፡ ብርታትም በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ለተቀመጠው ለነበረው ፡ ላለው ፡ ለሚመለሰው ለታረደው ፡ በግ ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው (፬x) ከሽማግሌዎቹም ፡ አንዱ ፡ ተመልሶ እንዚህ ፡ ነጩን ፡ ልብስ ፡ የለበሱ ፡ እነማን ፡ ናቸው ከወዴትስ ፡ መጡ ፡ አለኝ እኔም ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ ታውቃለህ ፡ አልኩት አለኝም ፡ እነዚህ ፡ ከታላቁ ፡ መከራ ፡ የመጡ ፡ ናቸው ልብሳቸውንም ፡ አጥበው ፡ በበጉ ፡ ደም ፡ አነጹ ስለዚህ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ዙፋን ፡ ፊት ፡ አሉ ሌሊትና ፡ ቀንም ፡ በመቅደሱ ፡ ያመልኩታል በዙፋኑም ፡ ላይ ፡ የተቀመጠው ፡ በእነርሱ ፡ ላይ ፡ ያድርባቸዋል ከእንግዲህ ፡ ወዲስ ፡ አይራቡም ፡ ከእንግዲህም ፡ ወዲህ ፡ አይጠሙም ፀሐይም ፡ ትኩሳትም ፡ ሁሉም ፡ ከቶ ፡ አይወርድባቸውም በዙፋኑ ፡ መካከል ፡ ያለው ፡ በጉ ፡ እረኛቸው ፡ ይሆናልና ወደ ፡ ሕይወትም ፡ ውኃ ፡ ምንጭ ፡ ይመራቸዋልና እግዚአብሔርም ፡ እምባዎችን ፡ ሁሉ ፡ ከዓይናቸው ፡ ያብሳል [4] ከታላቅ ፡ መከራ ፡ የመጡ ፡ ናቸው በበጉ ፡ ደምም ፡ አነጹ ፡ ልብሳቸውን በዙፋኑ ፡ ፊት ፡ ሌት ፡ ተቀን ፡ አሉ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እያሉ አዝ፦ በረከትና ፡ ክብርም ፡ ጥበብም ባለጸግነት ፡ ኃይልም ፡ ብርታትም በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ለተቀመጠው ለነበረው ፡ ላለው ፡ ለሚመለሰው ለታረደው ፡ በግ ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው (፬x)