Loading
Singer
ልዑል ፡ ነህ ፡ ተብሎ ፡ በፈርዖን ፡ ቤት ስፍራው ፡ እንዳልሆነ ፡ ሲገባው ፡ እውነት ሁሉን ፡ ክብር ፡ ትቶ ፡ መረጠ ፡ መከራ ተስማማ ፡ ጨክኖ ፡ ከፈጣሪው ፡ ጋራ (፪x) በዐይን ፡ ከሚታየው ፡ ይልቅ ፡ የማይታየውን ፡ አምኖ የዘለዓለም ፡ መታመኛው ፡ መኖሪያው ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆኖ ተሰደደ ፡ ሁሉን ፡ ትቶ ፡ ችግር ፡ መከራን ፡ ሳይፈራ በእውነት ፡ አድርጓልና ፡ መንገዱን ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ጋራ (አመነ ፡ እግዚአብሔርን ፡ አመነ) በትህትና ፡ ታዘዘ (ለእውነት ፡ ለመታዘዝ ፡ ጨከነ) ወደ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ተጓዘ (አመነ ፡ እግዚአብሔርን ፡ አመነ) ትኩር ፡ ብሎ ፡ አይቶ ፡ የሩቁን (ለእውነት ፡ ለመታዘዝ ፡ ጨከነ) የተጠበቀለት ፡ እርስቱን (አመነ ፡ እግዚአብሔርን ፡ አመነ) በእውነት ፡ እግዚአብሔር ፡ ይታመናል (፬x) ዛሬም ፡ ዋጋውን ፡ ተምኖ ፡ ከልቡ ፡ ታዛዥ ፡ የሆነ ከመልካም ፡ ነገር ፡ አይጐድልም ፡ ለአምላኩ ፡ የታመነ ምንም ፡ ፈተናው ፡ ቢበዛ ፡ የጊዜው ፡ ችግር ፡ መከራ በአሸናፊነት ፡ ይኖራል ፡ የሕይወት ፡ ፍሬ ፡ እያፈራ (በእውነት ፡ እግዚአብሔር ፡ ይታመናል) ለጥሪው ፡ ምላሽ ፡ ለሰጠ (እንዳለው ፡ እንደ ፡ ቃሉ ፡ ያደርጋል) በነፍሱ ፡ ሳይቀር ፡ ለቆረጠ (በእውነት ፡ እግዚአብሔር ፡ ይታመናል) የድል ፡ አክሊል ፡ ሽልማት (እንዳለው ፡ እንደ ፡ ቃሉ ፡ ያደርጋል) አይቀርም ፡ በጊዜው ፡ በወቅቱ (እንዳለው ፡ እንደ ፡ ቃሉ) በእውነት ፡ እግዚአብሔር ፡ ይታመናል (፬x) በኀጢአት ፡ ከሚገኘው ፡ ደስታ ፡ ይሻላል ፡ ታምኖ ፡ መኖር ፡ በጌታ የፈርዖንን ፡ ሹመት ፡ ተረድቶ ፡ ተሰደደ ፡ ሙሴ ፡ ክርስቶስን ፡ መርጦ ምን ፡ ቢበዛ ፡ መከራና ፡ ስደቱ ፡ በሰማይ ፡ የድል ፡ አክሊል ፡ ነው ፡ ሽልማቱ