Loading
Singer
የሠራዊት ፡ ጌታ ፡ ኃያሉ ፡ መድህኔ ሲጠብቀኝ ፡ ሳለ ፡ ፍርድና ፡ ኩነኔ በኃጢአት ፡ ጣር ፡ ስኖር ፡ ተሳስሬ ከእስራቴ ፡ ፈታኝ ፡ መራኝ ፡ ወደ ፡ አገሬ (፪x) አዝ፦ በጭንቄ ፡ ተጨንቆ ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ ተሰቅሎ ላረባሁት ፡ ልጁ ፡ እንዲያ ፡ ተጐሳቁሎ ደሙን ፡ አፈሰሰ ፡ በፍቅሩ ፡ ተገዶ ሕይወቴን ፡ አዳናት ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ተዋርዶ (፪x) ፍፁም ፡ የማልረባ ፡ ማስተዋል ፡ የሌለኝ አዳኜን ፡ የማላውቅ ፡ ፍርድ ፡ የሚጠብቀኝ የሰይጣን ፡ ምርኮኛ ፡ ሸክም ፡ የተጫነኝ እንዲህ ፡ ያለሁ ፡ ነበር ፡ ጌታ ፡ ሳያገኘኝ (፪x) አዝ፦ በጭንቄ ፡ ተጨንቆ ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ ተሰቅሎ ላረባሁት ፡ ልጁ ፡ እንዲያ ፡ ተጐሳቁሎ ደሙን ፡ አፈሰሰ ፡ በፍቅሩ ፡ ተገዶ ሕይወቴን ፡ አዳናት ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ተዋርዶ (፪x) ፍርሃት ፡ መጠራጠር ፡ ክፋትና ፡ እርኩሰት ይወገድ ፡ ትዕቢት ፡ ቅናት ፡ ምቀኝነት ተንኮልና ፡ ውሸት ፡ ሀሜት ፡ ክፉ ፡ ምኞት ተደምስሰው ፡ ይጥፉ ፡ በጽዮኑ ፡ አለት (፪x) ይውደቁ ፡ ይፈጩ ፡ ይድቀቁ ፡ በአንድነት ቀንበሩ ፡ ተሰብሯል ፡ ይቅርብኝ ፡ ባርነት ዕዳዬም ፡ ተከፍሎ ፡ ታውጇል ፡ አርነት ሞትም ፡ አያስፈራኝ ፡ ተሰጥቶኛል ፡ ሕይወት (፪x)