Loading
Singer
አምላኬማ ፡ አምላክ ፡ ነውና ፡ ዛሬም ፡ ይኖራል ሳይለወጥ ፡ እየለወጠ ፡ ታሪክ ፡ ይሰራል አምላኬማ ፡ አምላክ ፡ ነውና ፡ ዛሬም ፡ ይኖራል ሳይቀየር ፡ እየቀየረ ፡ ታሪክ ፡ ይሰራል ይሰራል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ እጅ አይቻለሁኝ ፡ ሁሉን ፡ ሲያበጅ ይሰራል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ ቃል ያለ ፡ ምሰሶ ፡ ሰማይ ፡ ቆሟል ይሰራል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ እጅ አይቻለሁኝ ፡ ሁሉን ፡ ሲያበጅ ይሰራል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ ቃል ስንት ፡ ደካማ ፡ በዚያ ፡ ቆሟል አዝ፦ አቤት ፡ አቤት ፡ ሥራህ እኔስ ፡ ጌታ ፡ ወደድኩልህ/አየሁልህ (፪x) ስለ ፡ ጌታ ፡ የሚባል ፡ ብዙ ፡ ነገር ፡ ኖሮ እንዴት ፡ ልቤ ፡ ይግባ ፡ ሀዘን ፡ እንጉርጉሮ እንደሰው ፡ ልጅ ፡ ሀሳብ ፡ አይደለም ፡ መንገዱ ለበጎ ፡ ነው ፡ እንጀ ፡ እሱን ፡ ለወደዱ አዝ፦ አቤት ፡ አቤት ፡ ሥራህ እኔስ ፡ ጌታ ፡ ወደድኩልህ/አየሁልህ (፪x) ይሰራል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ እጅ አይቻለሁኝ ፡ ሁሉን ፡ ሲያበጅ ይሰራል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ ቃል ያለ ፡ ምሰሶ ፡ ሰማይ ፡ ቆሟል ይሰራል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ እጅ አይቻለሁኝ ፡ ሁሉን ፡ ሲያበጅ ይሰራል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ ቃል ስንት ፡ ደካማ ፡ በዚያ ፡ ቆሟል በመጀመሪያ ፡ በፍጥረት ፡ ዓለም ግዑዝም ፡ ሕያው ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ የለም ሁሉን ፡ ካመጣህ ፡ ከምንም ፡ ነገር ዛሬም ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ተናግረህ ፡ አይቀር አዝ፦ አቤት ፡ አቤት ፡ ሥራህ እኔስ ፡ ጌታ ፡ ወደድኩልህ/አየሁልህ (፪x) ይሰራል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ ሥም ወደ ፡ ላይ ፡ አይሄድም ፡ ደፍሮ ፡ ማንም ይሰራል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ መንፈስ ወደ ፡ እውነት ፡ ሁሉ ፡ መርቶ ፡ ሚመልስ ይሰራል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ ሕግ ፍትህ ፡ ያለበት ፡ ፍርድ ፡ የሚያደርግ አዝ፦ አቤት ፡ አቤት ፡ ሥራህ እኔስ ፡ ጌታ ፡ ወደድኩልህ/አየሁልህ (፪x) የተዋበና ፡ የተራቀቀ የአምላኬ ፡ ሥራ ፡ እጅግ ፡ የላቀ መፈጠር ፡ እንጂ ፡ መፍጠር ፡ ማን ፡ ችሏል ማደስ ፡ ብቻ ፡ አይደል ፡ አዲስ ፡ ይሰራል አዝ፦ አቤት ፡ አቤት ፡ ሥራህ እኔስ ፡ ጌታ ፡ ወደድኩልህ/አየሁልህ (፪x)