Loading
Singer
የሰማይ ፡ አምላክ ፡ የሰራዊት ፡ ጌታ ነፍሴ ፡ ታመስግንህ ፡ ጥዋትና ፡ ማታ ቅኔ ፡ ልቀኝልህ ፡ ልቅረብ ፡ በዝማሬ በአንተ ፡ ስራ ፡ ነው ፡ እዚህ ፡ ያለሁት ፡ ዛሬ ዋጋ ፡ ያልነበረኝ ፡ ከንቱ ፡ የተረሳሁ አምላኬን ፡ የማላውቅ ፡ ነበርኩ ፡ እረኛ ፡ ያጣሁ በከበረው ፡ ልጅህ ፡ በደምህ ፡ ገዝተኸኝ አምላኬ ፡ ሆንክልኝ ፡ ልጅህ ፡ አደረከኝ መች ፡ አምላኬ ፡ ብቻ ፡ አበቴም ፡ ወዳጄም አስተማሪዬም ፡ ነው ፡ ጠባቂ ፡ እረኛዬም ሳዝን ፡ አጽናኜ ፡ ነው ፡ ሳጠፋም ፡ ቀጪዬ በመንገዴ ፡ ሁሉ ፡ ብርሃኔ ፡ መሪዬ ሞገሴም ፡ ነው ፡ ክብሬ ፡ ዕውቀቴ ፡ ጥበቤ መብራቴ ፡ ነው ፡ ለኔ ፡ ሆኖ ፡ ካጠገቤ ቢያመኝ ፡ መድሃኒቴ ፡ ወዜም ፡ ደም ፡ ግባቴ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ለኔ ፡ ዋስትና ፡ ለሕይወቴ የድህንነት ፡ ዋጋ ፡ ለኔ ፡ የከፈለው ውድ ፡ ነው ፡ ክቡር ፡ ነው ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው መቼ ፡ በዚህ ፡ ብቻ ፡ ተወኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ለሥጋም ፡ ለነፍሴም ፡ ሆነልኝ ፡ እርካታ