Loading
Singer
አዝ፦ ሰው ፡ በምን ፡ ይረካል ፡ ልቡ ዓለሙም ፡ አያልፍም ፡ ልኩ ጌታ ፡ ነው ፡ የሰላም ፡ ጥጉ (፪x) ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የደስታ ፡ ጥጉ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የደስታ ፡ ጥጉ (፪x) ልብህ ፡ ሲፈካ ፡ እንደ ፡ አበባ በአገኘው ፡ ነገር ፡ ሲፅናና ደግሞ ፡ በዚያው ፡ ልክ ፡ የሃዘን ፡ ድባብ ድብት ፡ ሲያደርገው ፡ ተስፋ ፡ ሲቆርጥ ስንቱ ፡ ነው ፡ ሚታየው ፡ በሕይወት ለዚያች ፡ ዕድሜ ፡ ተችሮት ግን ፡ አዋቂ ፡ ያ ፡ ብልሁ በአምላክ ፡ ሲሆን ፡ ነው ፡ መደሰቱ የማይናወጥ ፡ ሰላሜን ፡ ደስታዬን እኔ ፡ አግኝቻለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬን የምድር ፡ ስኬት ፡ ሚሰጠው ፡ ምንድን ፡ ነው ከኢየሱስ ፡ ሌላ ፡ ደስታ ፡ አለ ፡ ባይ ፡ ማን ፡ ነው አዝ፦ ሰው ፡ በምን ፡ ይረካል ፡ ልቡ ዓለሙም ፡ አያልፍም ፡ ልኩ ጌታ ፡ ነው ፡ የሰላም ፡ ጥጉ (፪x) ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የደስታ ፡ ጥጉ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የደስታ ፡ ጥጉ (፪x) መች ፡ በአንድ ፡ ነገር ፡ ልብ ፡ ይረካል አንዱ ፡ ሲሰጠው ፡ ሌላ ፡ ይሻል ያሻውንም ፡ ቢያገኝ ፡ ሰው ፡ ምኞቱ በቃ ፡ አይልም ፡ አይሞላለት ፡ ቋቱ ሕይወት ፡ የሚረጋው ፡ በእረፍት ኢየሱስ ፡ ሲገባ ፡ ወደ ፡ ቤት የሰላም ፡ ምንጩን ፡ ከተጠጉ ሌላ ፡ ደስታ ፡ አይፈልጉ የማይናወጥ ፡ ሰላሜን ፡ ደስታዬን እኔ ፡ አግኝቻለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬን የምድር ፡ ስኬት ፡ ይሰጠው ፡ ምንድን ፡ ነው ከኢየሱስ ፡ ሌላ ፡ ደስታ ፡ አለ ፡ ባይ ፡ ማን ፡ ነው (፪x) አዝ፦ ሰው ፡ በምን ፡ ይረካል ፡ ልቡ ዓለሙም ፡ አያልፍም ፡ ልኩ ጌታ ፡ ነው ፡ የሰላም ፡ ጥጉ (፪x) ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የደስታ ፡ ጥጉ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የደስታ ፡ ጥጉ (፪x)