Loading
Singer
አመንዝራዪቷ ፡ እንዲፈረድባት ፡ በጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ፊት ፡ አምጥተው ፡ አቆሟት ጌታ ፡ ግን ፡ ከእናንተ ፡ ሃጥያት ፡ የሌለበት አላቸው ፡ ይህቺን ፡ ሴት ፡ በድንጋይ ፡ ይውገራት ሁሉም ፡ ህሊናቸው ፡ ስለወቀሳቸው ወጡ ፡ ኢየሱስ ፡ ቀረ ፡ ያለሃጥያት ፡ ለብቻው ያቺ ፡ ሴት ፡ በፊቱ ፡ ቆማ ፡ ሲመለከት እኔ ፡ አልፈርድብሽም ፡ ደግመሽ ፡ አጢያት ፡ አትስሪ ፡ አላት የኢየሱስ ፡ ፍቅሩ ፡ ምህረቱ ፡ አዳናት በእግሩ ፡ ስር ፡ አረፈች ፡ ሰላም ፡ ስለሆናት ዋጋው ፡ እጅግ ፡ የብዛ ፡ ሽቶ ፡ የሞላበት የአልባጥሮስ ፡ ብልቃት ፡ ሰብራ ፡ አፈሰሰችለት ፡ የሰላም ፡ አምላክ ፡ የሰላም ፡ ንጉሥ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ኦ ፡ ኢየሱስ ምልካም ፡ ነህ ፡ ፍቅር ፡ ነህ ለሰው ፡ ሁሉ ፡ ትሆናለህ መልካም ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ፍቅር ፡ ነህ ፡ ለሰው ፡ ሁሉ ፡ ፡ መድሃኒት ፡ ነህ ርኩስ ፡ መንፈስ ፡ ይዞት ፡ ብረት ፡ የማያስረው ከሰው ፡ ተለይቶ ፡ መቃብር ፡ ሚኖረው የሰላሙ ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ ፡ ሲገናኘው እርኩስ ፡ መንፈሱን ፡ አዞ ፡ ገስጾ ፡ አስወጣው የዚህም ፡ ሰው ፡ ልቡ ፡ ተመለሰለት ከሰው ፡ ቀላቀለው ፡ ጌታ ፡ ነጻ ፡ አድርጐት ሚቀርበው ፡ ያልነበረውን ፡ ምስራች ፡ ነጋሪ ኢየሱስ ፡ አደረገው ፡ የእርሱን ፡ ድንቅ ፡ አብሳሪ ሽባው ፡ ተፈውሶ ፡ እውሮችም ፡ አይተው ደንቆሮችም ፡ ሰምተው ፡ ለምጻሞችም ፡ ነጽተው ነፍሳቸውም ፡ ድና ፡ ከስውም ፡ እኩል ፡ ሆነው ከበሩ ፡ በኢየሱስ ፡ ፡ ሆኖ ፡ የተጻፈው ልሸከመው ፡ ማልችለውን ፡ ከባዱን ፡ ኃጢአቴን ፡ የሰሱስ ፡ ተሸክሞ ፡ ሞቶልኛል ፡ ሞቴን እዳዬን ፡ ከፍሎልኝ ፡ ደሙ ፡ ደምስሶልኝ በዘለዓለም ፡ መጽሐፍ ፡ ስሜ ፡ ተጻፈልኝ የማይጠፋ ፡ ደስታ ፡ የማይወሰድብኝ ፈሰሰ ፡ በልቤ ፡ ኢየሱስ ፡ ፈውሶኝ የእርሱ ፡ የሆነውን ፡ የዘላላም ፡ ሰላም ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሰጠኝ ፡ ያልሆነ ፡ ከዚህ ፡ ዓለም የሰላሙ ፡ ንጉሥ ፡ የሰላሙ ፡ አለቃ ንጉሤ ፡ ሆናልኝ ፡ መቅበዝዜ ፡ አበቃ እፎይ ፡ አልኩ ፡ አረፍኩኝ ፡ እኔም ፡ እንደ ፡ ማሪያም ኢየሱስ ፡ ስለሆነኝ ፡ የሕይወቴ ፡ ሰላም