Loading
ህልመኛ ፡ ነኝ ፡ ህልም ፡ አለኝ ፡ የማያስቀምጠኝ ባሳብኩት ፡ ቁጥር ፡ ውስጤን ፡ የሚያዘልለኝ ለሌላው ፡ ባዋየው ፡ ቀድሞን ፡ ሁሌ ፡ ላይረዳኝ ቀባጣሪ ፡ አስመሰለኝ ፡ ነገሬን ፡ ሲሰማኝ ሁሁሁ ፡ አይ ፡ አይ (፪x) እኖር ፡ ነበር ፡ በተከለለች ፡ ትንሽ ፡ ሜዳ ትኩስ ፡ አየር ፡ ሲገባ ፡ ተሰማኝ ፡ በቅጥሩ ፡ ቀዳዳ ተስፋ ፡ መልዕክት ፡ ይዞ ፡ ነው ፡ የመጣው ፡ ወደ ፡ እኔ ሰብሬ ፡ የመውጣቴ ፡ ዛሬ ፡ ነው ፡ ቀኔ ሁሁሁ ፡ አይ ፡ አይ (፪x) (ማነው ፡ ያለው) አይሳካልሽም (ማነው ፡ ያለው) መድረሻ ፡ የለሽም (ማነው ፡ ያለው) ፍሬያማ ፡ አትሆኝም (ማነው ፡ ያለው) ለሌላው ፡ አተርፊም ይሳካል ፡ ይሆናል (፫x) ለሚያምን ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል (፫x) ምንም ፡ የሚያቅተኝ ፡ የለም ፡ ለእኔ ለሚያምን ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል (፫x) ምንም ፡ የሚያቅተኝ ፡ የለም ፡ ለእኔ እንደ ፡ ንስር ፡ ክንፍ ፡ አውጥቼ??? እበራለሁ ፡ የኋላዬን ፡ ትቼ እበራለሁ ፡ የኋላዬን ፡ ትቼ ምንም ፡ የሚያቅተኝ ፡ የለም ፡ ለእኔ (፫x) ምንም ፡ የሚያቅተኝ ፡ የለም ፡ ለእኔ (ማነው ፡ ያለው) አይሳካልሽም (ማነው ፡ ያለው) መድረሻ ፡ የለሽም (ማነው ፡ ያለው) ፍሬያማ ፡ አትሆኝም (ማነው ፡ ያለው) ለሌላው ፡ አተርፊም (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.