Loading
Singer
አዝ፦ ኢየሩሳሌም ፡ ቅድስቲት ፡ ከተማ የጐዳናሽ ፡ ውጥንቅጡ ፡ ቢበዛ ፡ እንኳ ሳላይሽ ፡ አልቀርም ፡ በአምላክ ፡ ኃይል ፡ እርዳታ (፪x) የናፈቀኝ ፡ ዜማ ፡ የቅዱስ ፡ ዝማሬ (፪x) አልቀርም ፡ ሳልዘምር ፡ ከጻድቃን ፡ አብሬ ከበጉ ፡ ዙፋን ፡ ሥር ፡ ሳልዞር ፡ በደስታ (፪x) አልቀርም ፡ ሳላይሽ ፡ አንቺ ፡ ቅዱስ ፡ ቦታ ማቋረጫው ፡ መንገድ ፡ ሊጠልፈኝ ፡ ቢነሳ (፪x) ሳላየው ፡ አልቀርም ፡ የይሁዳን ፡ አንበሳ ብቻዬን ፡ ብቀርም ፡ መንገደኛው ፡ ሸሽቶ (፪x) ሳላየው ፡ አልቀርም ፡ ኢየሱሴ ፡ መጥቶ የመናኝ ፡ ተራራን ፡ መቧጠጥ ፡ ቢያቅተኝ (፪x) የበረሃው ፡ ጉዞ ፡ ውኃ ፡ ጥም ፡ ቢጐዳኝ የሚያረካው ፡ ጌታ ፡ ሲመጣ ፡ ከሰማይ (፪x) ይረዳኛል ፡ በርግጥ ፡ ያቺን ፡ ቦታ ፡ እንዳይ አዝ፦ ኢየሩሳሌም ፡ ቅድስቲት ፡ ከተማ የጐዳናሽ ፡ ውጥንቅጡ ፡ ቢበዛ ፡ እንኳ ሳላይሽ ፡ አልቀርም ፡ በአምላክ ፡ ኃይል ፡ እርዳታ (፪x) ኢየሩሳሌም ፡ ኢየሩሳሌም ፡ ኢየሩሳሌም ፡ አዲስ ፡ ሕይወት በድል ፡ ዳግም ፡ የምናይሽ ፡ የምንወርስሽ ፡ መቼ ፡ ይሆን አይቀር ፡ ቁርጥ ፡ ነው (፫x) ማረፊያችን ፡ እፎይታችን ፡ ስንወርስሽ ፡ ነው (፪x)