Loading
ከአንተ ፡ በፊት ፡ የቆሰሉ ፡ ብዙ ፡ አሉ ፡ ለወንጌሉ እንደ ፡ እኔና ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ በነጻነት ፡ ዘመን ፡ ያልተፈጠሩ ከአንቺ ፡ በፊት ፡ የተሰዉ ፡ ብዙ ፡ አሉ ፡ ለወንጌሉ እንደ ፡ እኔና ፡ እንደ ፡ አንቺ ፡ በነጻነት ፡ ዘመን ፡ ያልተፈጠሩ ከእኛ ፡ በፊት ፡ ብዙ ፡ አሉ ፡ የተሰዉ ፡ ለወንጌሉ እንደ ፡ እኛ ፡ በነጻነት ፡ ዘመን ፡ ያልተፈጠሩ ሳይሉ ፡ እጅ ፡ እግሬን ፡ ጨርቄን ፡ ማቄን ፡ በጽድቅ ፡ የኖሩ በጌታ ፡ የተጉ ፡ ለጌታ ፡ የኖሩ ፡ በሰው ፡ የተጠሉ አቤት ፡ የሮጡለትን ፡ ያዩታል ፡ ከወደላይ የክብሩ ፡ ጌታ ፡ ሲያከብራቸው ፡ በሠማይ አቤት ፡ ያዩታል ፡ ጌታን ፡ ፊት ፡ ለፊት ሳያዩት ፡ ያመኑትን ፡ የናፈቁትን በነፍሳቸው ፡ የጨከኑት ፡ በሥጋቸው ፡ ያከበሩት አይገኝም ፡ አክሊላቸው ፡ በሠማይ ፡ ነው ፡ ክፍያቸው አቤት ፡ የሮጡለትን ፡ ያዩታል ፡ ከወደላይ ሆነው ፡ የባርነት ፡ ባሪያ ፡ ወጥተው ፡ ከሰውነት ፡ ተራ የእኔ ፡ የሚሉት ፡ የሌላቸው ፡ ልሩጥ ፡ ለእኔም ፡ ማያቃቸው ለወንጌል ፡ የቆሙ ፡ ለወንጌል ፡ የቀኑ ገንዘብ ፡ የማይደፍራቸው ፡ ሰልፍ ፡ ብርታታቸው አቤት ፡ የሮጡለትን ፡ ያዩታል ፡ ከወደላይ የክብሩ ፡ ጌታ ፡ ሲያከብራቸው ፡ በሠማይ አቤት ፡ ያዩታል ፡ ጌታን ፡ ፊት ፡ ለፊት ሳያዩት ፡ ያመኑትን ፡ የናፈቁት በነፍሳቸው ፡ የጨከኑት ፡ በሥጋቸው ፡ ያከበሩት አይገኝም ፡ አክሊላቸው ፡ በሠማይ ፡ ነው ፡ ክፍያቸው አቤት ፡ ያዩታል ፡ ጌታን ፡ ፊት ፡ ለፊት ማነው ፡ ታዲያ ፡ የዘመኔ ፡ አርበኛ ለጌታ ፡ ነገር ፡ ያልተኛ ብድራቱን ፡ እዚህ ፡ ያልተቀበለ እውነት ፡ ለወንጌል ፡ የጨከነ በነጻነት ፡ ዘመን ፡ ራሱን ፡ የሰዋ ለጥቅም ፡ ያልኖረ ፡ በእምነቱ ፡ የጸና ማነው ፡ የዘመኔ ፡ ወንጌል ፡ ነጋሪ በተግባር ፡ የታየ ፡ የጽድቅ ፡ ተባባሪ ያልሆነ ፡ በፍፁም ፡ የነጻነት ፡ ባሪያ ከቶ ፡ ያልተገኘ ፡ እዚህ ፡ ሲሉት ፡ እዚያ ማነው ፡ የአቋም ፡ ሰው ፡ ዘመን ፡ ተሻጋሪ ሰልፍ ፡ እየበረታ ፡ ወንጌሉን ፡ ዘማሪ ማነው ፡ የዘመኔ ፡ ባለ ፡ አክሊል ፡ ተረኛ ለራሱ ፡ ያልኖረ ፡ ከሥጋው ፡ ጠበኛ ሞትን ፡ ጥቅሜ ፡ ብሎ ፡ በነፍሱ ፡ የጨከነ ግራ ፡ ቀኝ ፡ ያላየ ፡ ለቃሉ ፡ የታመነ ማነው ፡ የዘመኔ ፡ አርበኛ ፡ ማነው አቤት ፡ የሮጡለትም ፡ ያዩታል ፡ ከወደላይ የክብሩ ፡ ጌታ ፡ ሲያከብራቸው ፡ በሠማይ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.