Loading
Singer
ትላንት ፡ የረዳኝ ፡ ዛሬም ፡ ሚረዳኝ ጌታን ፡ ይዣለሁ ፡ ምን ፡ አሰጋኝ X፪ አለ ፡ ጌታ X፰ ባለፀጋው ፡ ኢየሱስ ፡ አባቴ ምንጬ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ በረከቴ ከቶ ፡ አልሰጋም ፡ ምን ፡ እሆን ፡ ብዬ እኖራለሁ ፡ ተዘልዬ X፪ መከራና ፡ ችግሩ ፡ ውጊያውም ፡ ቢበዛ ድል ፡ አድራጊው ፡ ኢየሱስ ፡ አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ያደርገዋል ፡ ጌታ ፡ የተናገረኝን አየዋለሁ ፡ ይሆናል ፡ ቃል ፡ የገባልኝን ያለኝን ፡ ልመነው ፡ ልመነው ፡ ልመነው ጌታዬ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ታማኝ ፡ ነው X፪ ትላንት ፡ የረዳኝ ፡ ዛሬም ፡ ሚረዳኝ ጌታን ፡ ይዣለሁ ፡ ምን ፡ አሰጋኝ X፪ አለ ፡ ጌታ X፰ ቃሉን ፡ ሰጥቶ ፡ ያስጠበቀኝ ከመንገድ ፡ ላይ ፡ መች ፡ ሊጥለኝ እወርሳለሁ ፡ ጌታን ፡ ታምኜ እሄዳለሁ ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ ሆኜ ፡ X፪ አባቶች ፡ አመኑት ፡ ደመናን ፡ ሳያዩ ተስፋ ፡ እድርገው ፡ ጌታን ፡ ከቶ ፡ መች ፡ አፈሩ በመጠበቂያዬ ፡ ላይ ፡ እጠብቀዋለሁ ዘንበል ፡ ይላል ፡ ጌታ ፡ ቃሉን ፡ ምን ፡ ሊያደርገው ያለኝን ፡ ልመነው ፡ ልመነው ፡ ልመነው ጌታዬ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ታማኝ ፡ ነው X፪