Loading
Singer
ከልጅነቴ ፡ ጀምሮ ፡ እጄን ፡ አጥብቆ ፡ የያዘኝ ዘር ፡ ባልተዘራበት ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ በፍቅሩ ፡ ያባበለኝ ጊንጡን ፡ ረጋግጦልኝ ፡ እባቡም ፡ እንዳይነድፈኝ እንባዬን ፡ በእጁ ፡ ጠራርጐ ፡ አባት ፡ ልሁንሽ ፡ ያለኝ አዝ፦ የራራልኝ ፡ የደገፈኝ ፡ ሰዎች ፡ ሲረሱኝ ፡ ያስታወሰኝ ዛሬም ፡ ሊረዳኝ ፡ መች ፡ ይሰለቻል በእርሱ ፡ ተረድቶ ፡ ማን ፡ ወድቆ ፡ ያውቃል (፪x) ይችላል ፡ ይችላል ፡ ብያለሁ ፡ በነገሬ ፡ ላይ ቃል ፡ ከአፉ ፡ ይውጣ ፡ እንጂ ፡ ከሠማይ የሞተው ፡ ይነሳ ፡ የለም ፡ ወይ ይችላል ፡ ይችላል ፡ ብያለሁ ፡ በነገሬ ፡ ላይ ቃል ፡ ከአፉ ፡ ይውጣ ፡ እንጂ ፡ ከሠማይ አልአዛርስ ፡ ቆሞ ፡ የለም ፡ ወይ በአመት ፡ መሃል ፡ ሁል ፡ ጊዜ ፡ የማይለወጥ ፡ ደግ ፡ ጌታ ተስፋ ፡ ሲጨልም ፡ ቀን ፡ ሲመሽ ፡ የሚደርስ የማታ ፡ ማታ ስሙን ፡ ጠርቼ ፡ አላፈርኩ ፡ አንገት ፡ አልደፋሁ ፡ በዘመኔ ህያው ፡ ምስክር ፡ ያረገኝ ፡ ሳይርቀኝ ፡ ቆሞ ፡ ከጐኔ አዝ፦ የራራልኝ ፡ የደገፈኝ ፡ ሰዎች ፡ ሲረሱኝ ፡ ያስታወሰኝ ዛሬም ፡ ሊረዳኝ ፡ መች ፡ ይሰለቻል በእርሱ ፡ ተረድቶ ፡ ማን ፡ ወድቆ ፡ ያውቃል (፪x) ይችላል ፡ ይችላል ፡ ብያለሁ ፡ በነገሬ ፡ ላይ ቃል ፡ ከአፉ ፡ ይውጣ ፡ እንጂ ፡ ከሠማይ የሞተው ፡ ይነሳል ፡ የለም ፡ ወይ ይችላል ፡ ይችላል ፡ ብያለሁ ፡ በነገሬ ፡ ላይ ቃል ፡ ከአፉ ፡ ይውጣ ፡ እንጂ ፡ ከሠማይ አልአዛርስ ፡ ቆሞ ፡ የለም ፡ ወይ የደረቀ ፡ አጥንት ፡ ነው ፡ ግን ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ቀላል ፡ ነው የሸተተ ፡ ሬሳ ፡ ነው ፡ ግን ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ቀላል ፡ ነው ትቼዋለሁ ፡ ቀብሬው ፡ ግን ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ቀላል ፡ ነው ያወጣዋል ፡ በጊዜው ፡ አዎ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ቀላል ፡ ነው መርከብ ፡ ተሰብሮ ፡ በተሰበረው መድረስ ፡ ከቻለ ፡ ያ ፡ የእምነት ፡ ሰው ዛሬም ፡ በቤቴ ፡ ይሄ ፡ ይሆናል አልጠረጥርም ፡ እርሱ ፡ ይችላል አልጠረጥርም ፡ እርሱ ፡ ይችላል አልጠረጥርም ፡ ጌታ ፡ ይችላል አልጠረጥርም ፡ ጌታ ፡ ይችላል አልጠረጥርም ፡ እርሱ ፡ ይችላል አዝ፦ የራራልኝ ፡ የደገፈኝ ፡ ሰዎች ፡ ሲረሱኝ ፡ ያስታወሰኝ ዛሬም ፡ ሊረዳኝ ፡ መች ፡ ይሰለቻል በእርሱ ፡ ተረድቶ ፡ ማን ፡ ወድቆ ፡ ያውቃል (፪x)