Loading
Singer
ኀጢአት ፡ መሆኑን ፡ እየተረዳን ፡ በደምብ ፡ አውቀነው የምንአለበት ፡ ተዉ ፡ ባክህን ፡ ብለን ፡ አለፍነው በስግ ፡ ስሜት ፡ እየተነዳን ፡ ስንሸፋፍነው ያወቅነው ፡ መስሎን ፡ እንዲያው ፡ በመላ ፡ የዘመኑ ፡ ሰው በሰንበት ፡ ብቻ ፡ ስንንመላለስ ፡ ልማድ ፡ ሆኖብን አይፈሪሳዊ ፡ እያለ ፡ ጌታ ፡ ግብዞች ፡ ሲለን እንደ ፡ መቃብር ፡ ከላይ ፡ ስንታይ ፡ ኖራ ፡ ተቀብተን ቅሚያና ፡ ዝርፊያ ፡ ውስጣችን ፡ ሞልቷል ፡ በመንፈስ ፡ ላየን አዝ፦ ይቅርብን ፡ እንተው ፣ ይቅርብን ፡ እንተው ለእኛ ፡ ሚሆነው ፡ ጌታ ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x) ትንኝ ፡ አጥርተው ፡ ግመል ፡ እየዋጡ ፡ ቢመላለርሱ የበግ ፡ ለምድ ፡ ለብሰው ፡ ለታይታ ፡ ብቻ ፡ ጻድቅ ፡ ቢመስሉም ጌታ ፡ ይመጣል ፡ በእጁ ፡ መርሽ ፡ ይዞ ፡ ቤቱን ፡ ሊያጠራ ዝም ፡ ብሎ ፡ አያይም ፡ በመቅደሱ ፡ ውስጥ ፡ ኀጢአት ፡ ሲደራ ስንዴና ፡ እንክርዳድ ፡ ጐተራ ፡ አይገባም ፡ ብደምብ ፡ ሳይጠራ ከመንጋው ፡ መሃል ፡ ቢመሳሰሉ ፡ ሆኖ ፡ በጋራ ጌታ ፡ ሳይለው ፡ ይህ ፡ ክርስቲያን ፡ ነው ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ቢለው መጋፋት ፡ አይደል ፡ የእርሱ ፡ መለኪያው ፡ ጌታን ፡ መኖር ፡ ነው አዝ፦ ይቅርብን ፡ እንተው ፣ ይቅርብን ፡ እንተው ለእኛ ፡ ሚሆነው ፡ ጌታ ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x) ምንም ፡ ቢማሩ ፡ ለውጥ ፡ ከሌለ ፡ መምህር ፡ ቢባሉ አያስደንቅም ፡ ወረቀት ፡ ይዘው ፡ ዲግሪ ፡ ቢጭኑ አንቱ ፡ ቢባሉ ፡ ለምን ፡ ይጠቅማል ፡ ሕይወት ፡ ከሌለው ዝናና ፡ ክብር ፡ በምድር ፡ ያለው ፡ ሁሉም ፡ ጠፊ ፡ ነው እንዲያው ፡ በጭፍር ፡ ምንም ፡ ሳይገባው ፡ የጌታ ፡ አላማው ቢሰብክ ፡ ቢዘምር ፡ ቃሉን ፡ አጣፍጦ ፡ ወደድኩህ ፡ ቢለው ለራሱ ፡ ክብር ፡ እያመቻቸ ፡ የኖረውን ፡ ሰው ተጠቀመብኝ ፡ አለ ፡ እንጂ ፡ እራሱ ፡ ጌታ ፡ መች ፡ አለ አዝ፦ ይቅርብን ፡ እንተው ፣ ይቅርብን ፡ እንተው ለእኛ ፡ ሚሆነው ፡ ጌታ ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)