Loading
Singer
አትተወኝ ፡ እባክህ ፡ አትራቀኝ መንፈስህን ፡ ከውስጤ ፡ አትውሰደው (፪x) ደግሞ ፡ እንደሚያውቅ እንደሚያውቅ ፡ ልብ ፡ እንዳለው ብዙ ፡ ደከምኩኝ ፡ እራሴን ፡ ታዝቤያለሁ (፪x) አዝ፦ ይቅርታ ፡ ይቅርታ የእኔ ፡ አባት ፡ ይቅርታ ይቅር ፡ በለኝና ፡ አስገባኝ ዳግም ፡ ወደ ፡ ጉያህ (፪x) ያኔ ፡ ያኔ ፡ አንተን ፡ ያወኩበት ፡ የልጅነት ፡ ኩራት አይደክመኝም ፡ ፊትህን ፡ ስፈልግ ፡ ጠዋት ፡ ሆነ ፡ ማታ ምነው ፡ አሁን ፡ ልቤን ፡ ምን ፡ አገኘው ፡ ምን ፡ ገባብኝ ቆም ፡ ብዬ ፡ ራሴን ፡ ልጠይቀው ፡ ምህረት ፡ አርግልኝ ወደ ፡ አይምሮዬ ፡ ልመለስና ማረኝ ፡ ልበለው ፡ በርከክ ፡ ልበልና (፪x) አዝ፦ ይቅርታ ፡ ይቅርታ የእኔ ፡ አባት ፡ ይቅርታ ይቅር ፡ በለኝና ፡ አስገባኝ ዳግም ፡ ወደ ፡ ጉያህ (፪x)