Loading
ሰው ፡ መሆኑን ፡ አይደል ፡ ልብሱን ፡ አከበረ ሰው ፡ በገንዘቡ ፡ ልክ ፡ ወዳጅ ፡ አስቆጠረ (አቤት ፡ አቤት) ምስኪኑ ፡ ሲመጣ ፡ አጥቶ ፡ የሚቀምሰው የሚቀርበው ፡ ጠፍቶ ፡ ፍቅር ፡ እንኳን ፡ ከራቀው አቤት ፡ አቤት ፡ አቤቱ ፡ ምን ፡ አልከው አዝ፦ አቤቱ ፡ አትታዘበን እንመለሳለን ፡ ይቅር ፡ በለን (፪x) ምሕረቱን ፡ ተማምነን ፡ አይተን ፡ እንደዋዛ የድፍረታችን ፡ ልክ ፡ ሃጥያታችን ፡ በዛ ታጋሽ ፡ ሳይፈርድብን ፡ ቁጣውን ፡ ሳይልከው ይብቃን ፡ እንመለስ ፡ ዝምታው ፡ ምክር ፡ ነው የቤትህ ፡ አገልጋይ ፡ ስንቱን ፡ ሕዝብ ፡ አሰረው የሚያወራው ፡ አፉ ፡ ልቡ ፡ ግን ፡ ሌላ ፡ ነው (አቤት ፡ አቤት) ተግባር ፡ የለሽ ፡ ምክሩ ፡ ለራሱም ፡ ካልበጀው ልጅ ፡ አባቱ ፡ ታሞ ፡ እንዴት ፡ ይመልሰው አቤት ፡ አቤት ፡ አቤቱ ፡ ምን ፡ አልከው አዝ፦ አቤቱ ፡ አትታዘበን እንመለሳለን ፡ ይቅር ፡ በለን (፪x) ያከበርከው ፡ ትዳር ፡ ያቀናኸው ፡ ጎጆ ሊዘልበት ፡ ጠላት ፡ ተንዶ ፡ ተንዶ (አቤት ፡ አቤት) እንደ ፡ አሸዋ ፡ ሲርድ ፡ ከአለት ፡ ያፀናኸው እሌላ ፡ ሲከጅል ፡ በክብር ፡ የዳርከው አቤት ፡ አቤት ፡ አቤቱ ፡ ምን ፡ አልከው ምሕረቱን ፡ ተማምነን ፡ አይተን ፡ እንደዋዛ የድፍረታችን ፡ ልክ ፡ ሃጥያታችን ፡ በዛ ታጋሽ ፡ ሳይፈርድብን ፡ ቁጣውን ፡ ሳይልከው ይብቃን ፡ እንመለስ ፡ ዝምታው ፡ ምክር ፡ ነው መስሎት ፡ የተማረ ፡ በልጦበት ፡ እውቀቱ አምላክ ፡ የለም ፡ አለኝ ፡ ኢኸው ፡ እንደልቡ ፡ ይህ ፡ ሰው (አቤት ፡ አቤት) የአመፃው ፡ ብዛት ፡ ሃጥያቱም ፡ ሲከፋ ሴት ፡ ለሴት ፡ ተዳረች ፡ ወንድም ፡ ወንድ ፡ አገባ አቤት ፡ አቤት ፡ አቤቱ ፡ ምን ፡ አልከው አዝ፦ አቤቱ ፡ አትታዘበን እንመለሳለን ፡ ይቅር ፡ በለን (፪x) ለተመቸው ፡ እርሙ ፡ መች ፡ ይቅርታን ፡ ያውቃል ይልቅ ፡ ለጥፋቱ ፡ ጥቅስ ፡ ይሸራርፋል ፡ ይህ ፡ ሰው ፡ አቤት ፡ አቤት መውጣቱስ ፡ ይክበደው ፡ አጠፋሁ ፡ ቢል ፡ ምነው እራስን ፡ አታሎ ፡ መጨረሻው ፡ የት ፡ ነው አቤት ፡ አቤት ፡ አቤቱ ፡ ምን ፡ አልከው ምሕረቱን ፡ ተማምነን ፡ አይተን ፡ እንደዋዛ የድፍረታችን ፡ ልክ ፡ ሃጥያታችን ፡ በዛ ታጋሽ ፡ ሳይፈርድብን ፡ ቁጣውን ፡ ሳይልከው ይብቃን ፡ እንመለስ ፡ ዝምታው ፡ ምክር ፡ ነው
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.