Loading
ስራመድ ፡ በሞት ፡ ጐዳና ድካሜን ፡ ከላይ ፡ አየና ለወጠው ፡ የኔን ፡ ፍፃሜ ላምልከው ፡ በቀረኝ ፡ ዕድሜ (፪x) ላምልከው ፡ በቀረኝ ፡ ዕድሜ (፬x) አዝ፦ ምሥጋናዬ ፡ ለአንተ ፡ ነው ዝማሬዬ ፡ ለአንተ ፡ ነው አምልኮዬ ፡ ለአንተ ፡ ነው የእኔን ፡ ክፉ ፡ ለማትወደው (፭x) ስከተል ፡ የማይጠቅመውን ሳላውቀው ፡ ክፉና ፡ ደጉን አንተ ፡ ነህ ፡ የሰበሰብከኝ ማረፊያ ፡ ጥላ ፡ የሆንከኝ (፭x) አዝ፦ ምሥጋናዬ ፡ ለአንተ ፡ ነው ዝማሬዬ ፡ ለአንተ ፡ ነው አምልኮዬ ፡ ለአንተ ፡ ነው የእኔን ፡ ክፉ ፡ ለማትወደው (፭x) ሳነባ ፡ ልቤ ፡ ሲከፋ ስጐተት ፡ በጠላት ፡ ተስፋ ሰው ፡ አይደል ፡ የደረሰልኝ እጅህ ፡ ነው ፡ ከሞት ፡ ያስጣለኝ (፭x) አዝ፦ ምሥጋናዬ ፡ ለአንተ ፡ ነው ዝማሬዬ ፡ ለአንተ ፡ ነው አምልኮዬ ፡ ለአንተ ፡ ነው የእኔን ፡ ክፉ ፡ ለማትወደው (፭x) ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ ለሥምህ ፡ ልዘምር ሁልጊዜ ፡ ሁልጊዜ ፡ ሁልጌዜ ፡ ላምልክህ ፡ ኢየሱሴ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አልኖር ፡ ከአንተ ፡ ርቄ ወዳጄ ፡ ወዳጄ ፡ ወዳጄ ፡ ላምልክህ ፡ ፈቅጄ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.