Loading
Singer
ተስፋዬ ፡ ተስፋዬ ፡ ነህ (፬x) አላማዬ ፡ ግቤ ፡ የቀን ፡ የለት ፡ ህልሜ መደምደሚያዬ ፡ ነህ ፡ ያለኸኝ ፡ ተስፋዬ (፪x) የእኔ ፡ ነገር ፡ አላበቃም ፡ ጌታ ፡ ካለ ፡ አላለቀም የእኔ ፡ ነገር ፡ አላበቃም ፡ ጌታ ፡ ካለ ፡ አላለቀም በእኔና ፡ ሞት ፡ መሃል ፡ ተስፋ ፡ አለኝ (፪x) አንድ ፡ እርምጃ ፡ ቀርቶኝ ፡ ተስፋ ፡ አለኝ (፪x) ስጋዬ ፡ እጅ ፡ ሰጥቶ ፡ ተስፋ ፡ አለኝ (፪x) ሰው ፡ ተስፋው ፡ ተሟጦ ፡ ተስፋ ፡ አለኝ (፪x) አዝ፦ የእኔ ፡ ነገር ፡ አላበቃም ጌታ ፡ ካለ ፡ አላለቀም (፪x) ቢቆረጥ ፡ ዛፍ ፡ ግንዱ ፡ ተስፋ ፡ አለ (፪x) የውሃ ፡ ሽታ ፡ ካለ ፡ ተስፋ ፡ አለ (፪x) ስሩ ፡ ጌታ ፡ ካለ ፡ ተስፋ ፡ አለ (፪x) አለቱ ፡ ላይ ፡ ላለ ፡ ተስፋ ፡ አለ (፪x) አዝ፦ የእኔ ፡ ነገር ፡ አላበቃም ጌታ ፡ ካለ ፡ አላለቀም (፪x) ቢሞት ፡ እንደአላዛር ፡ ተስፋ ፡ አለ (፪x) ቢገነዝ ፡ ቢታሰር ፡ ተስፋ ፡ አለ (፪x) ተከቶም ፡ ተቀብሮም ፡ ተስፋ ፡ አለ (፪x) አልቆ ፡ ተደምድሞ ፡ ተስፋ ፡ አለ (፪x) አዝ፦ የእኔ ፡ ነገር ፡ አላበቃም ጌታ ፡ ካለ ፡ አላለቀም (፪x)