Loading
የእኔ ፡ ምሥጋና ዝናብ ፡ እንደሌለው ፡ ደመና ውኃ ፡ እንደሌለው ፡ ደመና አይደለም ፡ የእኔ ፡ ምሥጋና (፪x) ወይ ፡ ዘንቦ ፡ ላይዘንብ ፡ ወይ ፡ ጥሎ ፡ ላይጥል መብረቁ ፡ ሲያስፈራ ፡ ሲል ፡ ብልጭ ፡ ድርግም (፪×) ነጐድጓዱ ፡ ታሞ ፡ ጠብ ፡ እንኳን ፡ ካላለ ዝናብ ፡ ፈርቶ ፡ ሰው ፡ ቤቱ ፡ ከዋለ ፡ ተታለለ ግርግር ፡ ባይኖር ፡ ሙዚቃ ፡ ባልሰማ የነፍሴ ፡ ምሥጋና ፡ ዙፋኑ ፡ ይሰማ ዝናብ ፡ እንደሌለው ፡ ደመና አይደለም ፡ የእኔ ፡ ምሥጋና የእኔ ፡ ምሥጋና ዝናብ ፡ እንደሌለው ፡ ደመና ውኃ ፡ እንደሌለው ፡ ደመና አይደለም ፡ የእኔ ፡ ምሥጋና እህሉ ፡ ሊበላሽ ፡ ዘንቦበት ፡ በረዶ እያለ ፡ ሲያወራ ፡ ካሁን ፡ አሁን ፡ ወርዶ ፡ በረዶ ጉሙ ፡ ሲያጉረጐርም ፡ መጣሁኝ ፡ እያለ ደመናው ፡ ሰንጥቆት ፡ ፀሐይ ፡ ብቅ ፡ ካለ ፡ ተታለለ ዝም ፡ ብዬ ፡ የምጮህ ፡ እንዲያው ፡ ባዶ ፡ ሜዳ አይደለሁም ፡ እኔስ ፡ ሞልቶኛል ፡ ምሥጋና ዝናብ ፡ እንደሌለው ፡ ደመና አይደለም ፡ የእኔ ፡ ምሥጋና ምሥጋና ፡ ምሥጋና (፪x) እሰዋለሁ ፡ ለጌታዬ ፡ ለአምላኬ ይገባዋልና ፡ በከፍታ ፡ በዝቅታ አምልኮዬን ፡ አቀርባለሁ ፡ ለእርሱ ፡ ክብር ፡ በደስታ ምሥጋና ፡ ምሥጋና (፪x) ለጌታዬ ፡ ለታደገኝ ፡ ለአዳነኝ ለክብሩ ፡ ዝቅ ፡ እያልኩኝ ፡ እየሰገድኩ ፡ እያመለኩ ፊቱ ፡ ብወድቅ ፡ ባደንቀው ፡ ባሞግሰው ፡ ለእርሱ ፡ አይበቃም የእኔ ፡ ምሥጋና ዝናብ ፡ እንደሌለው ፡ ደመና ውኃ ፡ እንደሌለው ፡ ደመና አይደለም ፡ የእኔ ፡ ምሥጋና (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.