Loading
Singer
አምላኬን ፡ ልባርክ ፡ አፌን ፡ እከፍታለሁ ለወደደኝ ፡ ጌታ ፡ ምስጋናን ፡ እሰዋለሁ ፡ ተመስገን ፡ እላለሁ በመከራ ፡ ጊዜ ፡ ፈጥኖ ፡ ደርሶልኛል ነፍሴ ፡ ትገዛለት ፡ ፍቅሩ ፡ አሸንፎኛል (፪x) ለመድህኔ ፡ ይሁን ፡ ምስጋና ድሃ ፡ አደጉን ፡ አስቧልና የሚያረካ ፡ ፈጸሞ ፡ በአለም እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ የለም አዝ:- ሰማይ ፡ ዙፋኑ ፡ መቀመጫው ምድርም ፡ ለእግሮቹ ፡ መረገጫ ስሙ ፡ ምን ፡ ጊዜም ፡ የሚረታ ትላንትም ፡ ዛሬም ፡ ነገም ፡ ጌታ የእኔ ፡ መድህን ፡ ጌታ ብርቱ ፡ መታጠቂያው ፡ ድንገት ፡ ሲላላበት የጦረኛው ፡ መውጊያው ፡ ጦር ፡ ሲሰበርበት (፪x) ተከላካይ ፡ ጋሻው ፡ ከእጁ ፡ ሲወድቅበት መከታ ፡ ነው ፡ ያለው ፡ ተገኔ ፡ ነው ፡ ያለው ፡ ምሽግ ፡ ሲናድበት መድህኔ ፡ ግን ፡ ሁሌ ፡ ባለ ፡ ድል ድል ፡ አድራጊ ፡ ክንዱ ፡ የማይዝል ታላቅ ፡ አምላክ ፡ የኔ ፡ መከታ ሁሌ ፡ የሚረታ አዝ:- ሰማይ ፡ ዙፋኑ ፡ መቀመጫው ምድርም ፡ ለእግሮቹ ፡ መረገጫ ስሙ ፡ ምንጊዜም ፡ የሚረታ ትላንትም ፡ ዛሬም ፡ ነገም ፡ ጌታ የእኔ ፡ መድህን ፡ ጌታ ሆ ፡ እየተባለ ፡ ተስፋ ፡ የተጣለበት በጊዜው ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ የተጋደለበት ፡ የተራረደበት ዛሬ ፡ ተረት ፡ ሆኖ ፡ በትዝብት ፡ ይወራል የኢየሱስ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ እያደር ፡ ያብባል ፡ እያደር ፡ ይጥማል የእግዚአብሄር ፡ ልጅ ፡ ሁሌ ፡ አሸናፊ የጠላቱን ፡ ድፍረት ፡ ገፋፊ በዙፋን ፡ ላይ ፡ ሁሌ ፡ የሚኖረው ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው አዝ:- ሰማይ ፡ ዙፋኑ ፡ መቀመጫው ምድርም ፡ ለእግሮቹ ፡ መረገጫ ስሙ ፡ ምንጊዜም ፡ የሚረታ ትላንትም ፡ ዛሬም ፡ ነገም ፡ ጌታ የእኔ ፡ መድህን ፡ ጌታ (፪x)