Loading
Singer
ጌቴ ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ቤዛ ጉስቁልናዬ ፡ ቢበዛ ከክብሩ ፡ ተዋረደልኝ በእኔ ፡ ፈንታ ፡ ታረደልኝ (፪x) አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ገዶት ኃጢአቴም ፡ አስጨንቆት ዝም ፡ ብሎ ፡ እንደ ፡ ጠቦት በሀሰት ፡ ተመስክሮበት ፡ በችሎት ዕዳዬን ፡ ከፍሎታል ፡ ተሰቅሎ ፡ በመሞት ግብዝ ፡ አይደል ፡ እንደ ፡ ሰው ወረት ፡ ጨርሶ ፡ ያልነካው በጐልጐታ ፡ ላይ ፡ የታየው እውነትም ፡ እርሱ ፡ ፍቅር ፡ ነው (፪x) አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ገዶት ኃጢአቴም ፡ አስጨንቆት ዝም ፡ ብሎ ፡ እንደ ፡ ጠቦት በሀሰት ፡ ተመስክሮበት ፡ በችሎት ዕዳዬን ፡ ከፍሎታል ፡ ተሰቅሎ ፡ በመሞት ያጀቡት ፡ ሁሉ ፡ ፈርጥጠው ለሰይፍ ፡ ለጐመድ ፡ አጋልጠው በዚያን ፡ ምሽት ፡ አልቦታል ቃቶ ፡ ነፍሴን ፡ ታድጓታል (፪x) አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ገዶት ኃጢአቴም ፡ አስጨንቆት ዝም ፡ ብሎ ፡ እንደ ፡ ጠቦት በሀሰት ፡ ተመስክሮበት ፡ በችሎት ዕዳዬን ፡ ከፍሎታል ፡ ተሰቅሎ ፡ በመሞት በግፍ ፡ ጀርባው ፡ ተላልጦ እግሩንም ፡ ለስቃይ ፡ ገልጦ ንጹስህ ፡ ደሙን ፡ ለእኔ ፡ ከፍሎ በቀራንዮ ፡ ደርቆ ፡ ውሎ (፪x) አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ገዶት ኃጢአቴም ፡ አስጨንቆት ዝም ፡ ብሎ ፡ እንደ ፡ ጠቦት በሀሰት ፡ ተመስክሮበት ፡ በችሎት ዕዳዬን ፡ ከፍሎታል ፡ ተሰቅሎ ፡ በመሞት ይህ ፡ ፍቅር ፡ በሕይወቴ ፡ ገብቶ የደህንነት ፡ ሥራ ፡ ሰርቶ ቆሻሻነቴን ፡ ቀይሮ አይቻለሁኝ ፡ ውብ ፡ ኑሮ (፪x) አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ገዶት ኃጢአቴም ፡ አስጨንቆት ዝም ፡ ብሎ ፡ እንደ ፡ ጠቦት በሀሰት ፡ ተመስክሮበት ፡ በችሎት ዕዳዬን ፡ ከፍሎታል ፡ ተሰቅሎ ፡ በመሞት