Loading
Singer
አገኘሁ ፡ መላ ፡ ያለበት ፡ ቤት አገኘሁ ፡ ፍርድ ፡ የሚሰጥበት ለዚህ ፡ ነው ፡ የተረጋጋሁት (፪x) ልዑል ፡ ነው ፡ ልዑል ፡ ነው ፡ አባቴ (፪x) ዝማሬው ፡ ይፈልቃል ፡ ከቤቴ እንዴት ፡ ይመኛል ፡ ልቤማ ፡ ሌላ ተስተናግጄ ፡ ከንጉሥ ፡ ጋራ ተቆረሰና ፡ የሰላም ፡ ማዕድ ቤቱ ፡ ይሞቃል ፡ አያስገባም ፡ ብርድ አሃ ፡ አሃ ፡ ለተጨነቀማ ፡ ግራ ፡ ለገባዉ ትክክለኛው ፡ መልስ ፡ በእጁ ፡ ነው ፡ ያለው (፪x) ተራራው ፡ ተጋርዶ ፡ ፊት ፡ ለፊት ፡ ሳየው ጌታ ፡ እንዳስለመደኝ ፡ እጄን ፡ አነሳሁ በመንፈስ ፡ የሆንን ፡ አምልኮን ፡ ስሰዋ የት ፡ እንደ ፡ ሄደ ፡ አላውቅም ፡ ወዴት ፡ እንደገባ የእኔ ፡ ጌታ ፡ የእኔ ፡ እረኛ ለዚህ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የጠራኛ/የቀባኛ (፪x) ሊነካኝ ፡ አይችልም ፡ ጠላቴ (፪x) እሳቱ ፡ ከቦኛል ፡ የአባቴ አትንኩት ፡ አትንኩት ፡ ይላሉ (፪x) ይታያል ፡ ደሙ ፡ በጉበኑ አትንኳት ፡ አትንኳት ፡ ይላሉ አትንኩት ፡ አትንኩት ፡ ይላሉ ይታያል ፡ ደሙ ፡ በጉበኑ ጳውሎስና ፡ ሲላስ ፡ ቢታሰር ፡ እጃቸው አምልኮ ፡ አላቆሙም ፡ ተፈቷል ፡ ውስጣቸው ሊጠፋ ፡ አይችልም ፡ ውስጥ ፡ ያለው ፡ እሳት እንደውም ፡ ይብሳል ፡ ሲቆሰቁስት የእኔ ፡ ጌታ ፡ የእኔ ፡ እረኛ ለዚህ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የቀባኛ/የጠራኛ (፪x) ወዴት ፡ ወዴት ፡ ወዴት (፪x) እንዴት ፡ እንዴት ፡ ይመኛል እንዴት ፡ እንዴት ፡ እንዴት የንጉሥ ፡ ቤተሰብ ፡ አይመኝም ፡ ሌላ አምሮበት ፡ ይኖራል ፡ ከእጁ ፡ እየበላ የንጉሥ ፡ ቤተሰብ ፡ አይመኝም ፡ ውጪ ያበድራል ፡ እንጂ ፡ አይደለም ፡ ተረጂ የእኔ ፡ ጌታ ፡ የእኔ ፡ እረኛ ለዚህ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የጠራኛ/የቀባኛ (፪x)