Loading
Singer
አዝ፦ የሚያበራ ፡ የንጋት ፡ ኮከብ ፡ የሆነ ከነገድም ፡ ከቋንቋ ፡ ሰዎችን ፡ ያዳነ የሞትና ፡ የሲዖልን ፡ መውጊያውን ፡ ሰብሮ ጠላትን ፡ ጠቢባንንም ፡ አሳፍሮ ዳግም ፡ ሊመጣ ፡ አለ ፡ በሰማይ ፡ ከብሮ የነገስታትን ፡ ኩራት ፡ ባዶ ፡ ያረገ ለምስኪኖች ፡ መንገሻ ፡ መንገድ ፡ ጠረገ የዚህችን ፡ አለም ፡ ጥበብ ፡ ለማሳፈር እኛን ፡ ሞኞች ፡ መረጠ ፡ ዘላለም ፡ ይክበር አዝ፦ የሚያበራ ፡ የንጋት ፡ ኮከብ ፡ የሆነ ከነገድም ፡ ከቋንቋ ፡ ሰዎችን ፡ ያዳነ የሞትና ፡ የሲዖልን ፡ መውጊያውን ፡ ሰብሮ ጠላትን ፡ ጠቢባንንም ፡ አሳፍሮ ዳግም ፡ ሊመጣ ፡ አለ ፡ በሰማይ ፡ ከብሮ ደረቱን ፡ በወርቅ ፡ መታጠቂያ ፡ ታጠቀ ጉስቁልናን ፡ ከልጆቹ ፡ አራቀ አኖቹ ፡ እንደ ፡ እሳት ፡ ነበልባል ፡ ናቸው ጨለማን ፡ ያስወገደ ፡ ክብሩን ፡ ታላቅ ፡ ነው አዝ፦ የሚያበራ ፡ የንጋት ፡ ኮከብ ፡ የሆነ ከነገድም ፡ ከቋንቋ ፡ ሰዎችን ፡ ያዳነ የሞትና ፡ የሲዖልን ፡ መውጊያውን ፡ ሰብሮ ጠላትን ፡ ጠቢባንንም ፡ አሳፍሮ ዳግም ፡ ሊመጣ ፡ አለ ፡ በሰማይ ፡ ከብሮ ከሰማይ ፡ በአመጻው ፡ የተወለደ በምድርም ፡ በሰዎች ፡ ላይ ፡ ሞት ፡ ያወረደ ኢየሱስ ፡ ከላይ ፡ ሲገለጥ ፡ የእኛ ፡ አባባ ጠላት ፡ የለም ፡ የታለ ፡ የት ፡ ፡ እንደ ፡ ገባ አዝ፦ የሚያበራ ፡ የንጋት ፡ ኮከብ ፡ የሆነ ከነገድም ፡ ከቋንቋ ፡ ሰዎችን ፡ ያዳነ የሞትና ፡ የሲዖልን ፡ መውጊያውን ፡ ሰብሮ ጠላትን ፡ ጠቢባንንም ፡ አሳፍሮ ዳግም ፡ ሊመጣ ፡ አለ ፡ በሰማይ ፡ ከብሮ በአራቱም ፡ ማዕዘናት ፡ ክብሩ ፡ እያበራ ውዳችን ፡ ይገለጣል ፡ ከመላዕክት ፡ ጋራ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ ስንሻገር ፡ ከአድማስ ፡ ወዲያ ተስፋችን ፡ ይፈጸማል ፡ ኦ ፡ ሃሌሉያ አዝ፦ የሚያበራ ፡ የንጋት ፡ ኮከብ ፡ የሆነ ከነገድም ፡ ከቋንቋ ፡ ሰዎችን ፡ ያዳነ የሞትና ፡ የሲዖልን ፡ መውጊያውን ፡ ሰብሮ ጠላትን ፡ ጠቢባንንም ፡ አሳፍሮ ዳግም ፡ ሊመጣ ፡ አለ ፡ በሰማይ ፡ ከብሮ