Loading
Singer
ነፍሴ ፡ በአንተ ፡ ሐሴት ፡ ታደርጋለች X፬ እግዚአብሔር ፡ የእኔ ፡ የእኔ ፡ ነው ፡ እያለች X፬ ዝማሬዋ ፡ ኃይሏ ፡ ጉልበት ፡ ሆነህላት ያለፈውን ፡ ዘመን ፡ ክንድህ ፡ አሻገራት አንተ ፡ ዘንድ ፡ እጅጉን ፡ ብዙ ፡ ኃይል ፡ አለና እስከፍጻሜውም ፡ በቤትህ ፡ ሚያጸና ነፍሴ ፡ በአንተ ፡ ሐሴት ፡ ታደርጋለች X፬ እግዚአብሔር ፡ የእኔ ፡ የእኔ ፡ ነው ፡ እያለች X፬ የእኔ ፡ የእኔ ፡ የእኔ ፡ የእኔ መመኪያዬ ፡ ሁሌ ፡ ክብሬ አንተ ፡ አይደለህ ፡ በዘመኔ የምጠራው ፡ ዘር ፡ ማንዘሬ ነፍሴ ፡ ምን ፡ አጣች ፡ አንተን ፡ አግኝታ ሆንክላት ፡ በጐ ፡ ሆንክላት ፡ ጋሻ ስለዚህ ፡ በእዚህ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ እንደዚህ ፡ ያምርብሻል ፡ ውዳሴ ፡ ምሥጋና ፡ ነፍሴ ፡ ስታፈልቂ ምንም ፡ የሌላትን ፡ ምንኛ ፡ ረዳሃት ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ እዚህ ፡ አደረስካት በአመራርህ ፡ ጌታ ፡ እጅግ ፡ እረክታለች አምላኬ ፡ መሪዬ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ ትላለች ነፍሴ ፡ በአንተ ፡ ሐሴት ፡ ታደርጋለች X፬ እግዚአብሔር ፡ የእኔ ፡ የእኔ ፡ ነው ፡ እያለች X፬ እግዚአብሔር ፡ ክብሬ ፡ ክብሬ ፡ ነው ፡ እያለች X፬