Loading
Singer
አዝ:- ዋስ ፡ ጠበቃዬ (፪x) ፡ ካህኔ ኢየሱስ ፡ የነፍስ ፡ አባቴ (፬x) የእርግብ ፡ የፍየል ፡ ደም ፡ ይፍሰስ መሰዊያ ፡ ላድርጋቸው ፡ እንድዱት የህዝቡ ፡ ኀጢአት ፡ እንዲሰረይለት ሚቃጠል ፡ መስዋዕት ፡ ይቅረብለት ይህ ፡ ስርአት ፡ ቀረ (፬x) መስዋዕቴ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆነ መስዋዕቴ ፡ የከበረ (፪x) አዝ:- ዋስ ፡ ጠበቃዬ (፪x) ፡ ካህኔ ኢየሱስ ፡ የነፍስ ፡ አባቴ (፬x) ኀጢአትን ፡ ማስወገድ ፡ የማይችሉ መስዋዕት ፡ ሁልጊዜ ፡ ሲያቅርቡ እርሱ ፡ ግን ፡ ለአንዴ ፡ ፈጽሞ ቀደሰኝ ፡ እራሱን ፡ አቅርቦ የአዲስ ፡ ኪዳን ፡ ልጅ ፡ ነኝ (፬x) የተሻለ ፡ ካህን ፡ አለኝ የተሻለ ፡ ኪዳን ፡ አለኝ (፪x) አዝ:- ዋስ ፡ ጠበቃዬ (፪x) ፡ ካህኔ ኢየሱስ ፡ የነፍስ ፡ አባቴ (፬x) ቃልኪዳን ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ አደረገ ህጉንም ፡ በልቤ ፡ አስቀመጠ በአዲስና ፡ በሕያው ፡ መንገድ አስገባኝ ፡ በስጋው ፡ በደም የአዲስ ፡ ኪዳን ፡ ልጅ ፡ ነኝ (፬x) የተሻለ ፡ ካህን ፡ አለኝ የተሻለ ፡ ኪዳን ፡ አለኝ (፪x) አዝ:- ዋስ ፡ ጠበቃዬ (፪x) ፡ ካህኔ ኢየሱስ ፡ የነፍስ ፡ አባቴ (፬x) እግዚአብሔር ፡ የራሱን ፡ ፍቅር ፡ የገለጠበት ስጦታው ፡ እንዴት ፡ ካለ ፡ ሞት ፡ እኔን ፡ ያዳነበት ተአምር ፡ የምለው ፡ በሕይወቴ ኢየሱሴ ፡ የነፍስ ፡ አባቴ ኦ ፡ ኢየሱሴ ፡ የነፍስ ፡ አባቴ (፪x) የውስጤን ፡ ሁሉ ፡ ማሳየው ፡ ሚስጥረኛዬ በአብ ፡ ቀኝ ፡ የሚቆምልኝ ፡ ጠበቃዬ ሚረዳኝ ፡ ደግሞም ፡ ሚረዳኝ ፡ ሊቀ ፡ ካህኔ ኢየሱሴ ፡ የነፍስ ፡ አባቴ ኦ ፡ ኢየሱሴ ፡ የነፍስ ፡ አባቴ (፮x)