Loading
Singer
የእኔ ፡ ደስታ ፡ ኢየሱስ አሃ ። የእኔ ፡ ዓለሜ ፡ የአንተ ፡ ክብር ፡ ነው /2/ የእኔ ፡ ዓለሜ ፡ የአንተ ፡ መንፈስ ፡ ነው /2/ የእኔ ፡ ዓለሜ ፡ የአንተ ፡ ክብር ፡ ነው /2/ የእኔ ፡ ዓለሜ ፡ የአንተ ፡ መንፈስ ፡ ነው /2/ የሰው ፡ ልጅ ፡ ምኞቱ ፡ ከፍታ ፡ ስኬቱ በመደረግ ፡ ያልፋል ፡ ሁሉም ፡ ነገር ፡ ከንቱ ሕይወት ፡ ተገለጠ ፡ ለእኔም ፡ በርቶልኛል ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ ያሻኛል ከአንተ ፡ ሌላ ፡ አያምረኝም /2/ ከአንተ ፡ ውጪ ፡ አያምረኝም /2/ ናፍቆቴ ፡ ነህ ፡ ምኞቴ ፡ ነህ ጉጉቴ ፡ ነህ ፡ ሕይወቴ ፡ ነህ የለም ፡ እንዳንተ ፡ ምወደው የለም ፡ እንዳንተ ፡ ምናፍቀው የለም ፡ እንዳንተ ፡ ምወደው የለም ፡ እንዳንተ ፡ ምናፍቀው በመንፈስ ፡ የሆነ ፡ ሰላም ፡ የሞላው ሃዘን ፡ የሌለበት ፡ የአንተ ፡ ዓለም ፡ ነው ዳግመኛ ፡ ብፈጠር ፡ እድሉን ፡ ባገኝ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የምታጓጓኝ ከአንተ ፡ ሌላ ፡ አያምረኝም /2/ ከአንተ ፡ ውጪ ፡ አያምረኝም /2/ የእኔ ፡ ዓለሜ ፡ የአንተ ፡ ክብር ፡ ነው /2/ የእኔ ፡ ዓለሜ ፡ የአንተ ፡ መንፈስ ፡ ነው /2/ የእኔ ፡ ዓለሜ ፡ የአንተ ፡ ክብር ፡ ነው /2/ የእኔ ፡ ዓለሜ ፡ የአንተ ፡ መንፈስ ፡ ነው /2/ አንተ ፡ ነህ ፡ ሰላም ፡ አንተ ፡ ነህ (የዚህ ፡ ቤት ፡ ሰላም ፡ የዚህ ፡ በቤት ፡ ክብር) ኢየሱስ ፡ (ኦሆሆ ፡ ሃሌሉያ)