Loading
Singer
ልፋ ያለው እንጨት - እድሉ የጠመመ ባሬላ ተብሎ - እየተሰየመ ያንን ኩንታል ድንጋይ - እየተሸከመ - ደግሞ ሌላው እንጨት - የ'ንጨት እድላሙ መስቀል ነህ ተብሎ - ተሰይሞ ስሙ አላፊ፣ አግዳሚ - እ'ሱን እንዲያስሙ ቀሳውስትን ቀጥሮ - በተቀባ ስሙ አንዱ የ'ንጨት ባሪያ - ሌላው የ'ንጨት ንጉስ ይሄ መሬት ሲስም - ያንኛው ሲኮፈስ 2x የተቀባው እንጨት - ካ'ናት ይሰቀላል ሌላ ታናሽ ረግጦ - በእንጨት መሰላል ካ'ናት ጋር እስኪደር - አንዱ ባ'ንዱ ልቆ በእንጨት ገበያ - እንጨት በ'ንጨት ደምቆ አንዱ የ'ንጨት ባሪያ - ሌላው የ'ንጨት ንጉስ ይሄ መሬት ሲስም - ያንኛው ሲኮፈስ 2x ቢያቃጥሉት አመድ - ቢቆርጡትም ጉቶ ቢለበለብ ከሰል - ጉቶነቱን ትቶ ለያይተነው እንጂ - ስሙን ሸልመነው ከንቱ ተሰባሪ - እንጨት ያው እንጨት ነው አንዱ የ'ንጨት ባሪያ - ሌላው የ'ንጨት ንጉስ ይሄ መሬት ሲስም - ያንኛው ሲኮፈስ 2x ምንም አንዱ ቢገን - ሌላው መሬት ቢልስ መፈራት ያለበት - የ'ንጭቶቹ ጌታ - በ'ሳት የሚመልስ 2x