Loading
Singer
አዝ፦ የወንድ ፡ ሙሸራ ፡ ድምጽ የሴት ፡ ሙሸራ ፡ ድምጽ "ቸር ፡ ነውና ፤ ቸር ፡ ነውና ምህረቱ ፡ ለዘለዓለም ፡ ነውና እግዚአብሔርን ፡ አመስግኑ" ፡ ይላሉ ሙሽሮቹ ፡ ይላሉ ፤ ሙሽሮቹ ፡ ይላሉ (፪x) እግዚአብሔር ፡ ቤትን ፡ ካልሰራ ፡ ሰው ፡ በከንቱ ፡ ይደክማል መሰረቱ ፡ ግን ፡ የሆነ ፡ ቤቱ ፡ ይጸናል ፡ ይቆማል ሁለትን ፡ ሰው ፡ አንድ ፡ የሚያደርግ ፡ ልዩ ፡ ችሎታ ፡ አለው ይህ ፡ ዕውቀቱ ፡ አሰራሩ ፡ ለእኛ ፡ እጅግ ፡ አስደናቂ ፡ ነው እድምተኞቻችን ፡ ብሉልን ፡ ጠጡልን ፡ ከሚሏቹህ ፡ ሌላ ቃል ፡ አላቸው ፡ ዛሬ ፡ አክብሩልን ፡ ብለው ፡ የጌቶቹን ፡ ጌታ ስንቱን ፡ አሳልፎ ፡ ቤት ፡ ለሰራላቸው ፡ ለዚህ ፡ መድሃኒያለም ከምሥጋና ፡ ሌላ ፡ የሚሰጠው ፡ የለም ከዕልልታ ፡ ሌላ ፡ የሚሰጠው ፡ የለም ከጭብጨባ ፡ ሌላ ፡ የሚሰጠው ፡ የለም ከዝማሬ ፡ ሌላ ፡ የሚሰጠው ፡ የለም አዝ፦ የወንድ ፡ ሙሸራ ፡ ድምጽ የሴት ፡ ሙሸራ ፡ ድምጽ "ቸር ፡ ነውና ፤ ቸር ፡ ነውና ምህረቱ ፡ ለዘለዓለም ፡ ነውና እግዚአብሔርን ፡ አመስግኑ" ፡ ይላሉ ሙሽሮቹ ፡ ይላሉ ፤ ሙሽሮቹ ፡ ይላሉ (፪x) የታመነ ፡ አምላክ ፡ በእራሱ ፡ መንገዱ ፡ ያስተሳሰራቸው ከአእምሮ ፡ በላይ ፡ በሆነው ፡ ጥበቡ ፡ ያገናኛቸው ከፀሐይ ፡ በታች ፡ ባገኙት ፡ በዕድሜ ፡ ዘመኖቻቸው ጌታ ፡ ይረዳናል ፡ እያሉ ፡ ጀመሩ ፡ ደስ ፡ እያላቸው ዛሬን ፡ የደስታ ፡ ቀን ፤ የጥምረት ፡ የሃሴት ፡ ንጉሥ ፡ ካደረገው ይህን ፡ አዲሱን ፡ ቤት ፤ ወዳጅ ፡ ቤተሰቦች ፡ አብረን ፡ እንመርቀው ሚስትን ፡ ያገኘ ፡ ሰው ፤ በረከት ፡ ካገኘ ፡ ሞገስ ፡ ከሆነለት እንዲህ ፡ ላደረገው ፡ ምሥጋና ፡ ይብዛለት እንዲህ ፡ ላደረገው ፡ ጭብጨባ ፡ ይብዛለት ይህን ፡ ላደረገው ፡ እስኪ ፡ ተቀኙለት ይህን ፡ ላደረገው ፡ ዕልልታ ፡ ይብዛለት አዝ፦ የወንድ ፡ ሙሸራ ፡ ድምጽ የሴት ፡ ሙሸራ ፡ ድምጽ "ቸር ፡ ነውና ፤ ቸር ፡ ነውና ምህረቱ ፡ ለዘለዓለም ፡ ነውና እግዚአብሔርን ፡ አመስግኑ" ፡ ይላሉ ሙሽሮቹ ፡ ይላሉ ፤ ሙሽሮቹ ፡ ይላሉ (፪x) ዛሬን ፡ የደስታ ፡ ቀን ፤ የጥምረት ፡ የሃሴት ፡ ንጉሥ ፡ ካደረገው ይህን ፡ አዲሱን ፡ ቤት ፤ ወዳጅ ፡ ቤተሰቦች ፡ አብረን ፡ እንመርቀው ሚስትን ፡ ያገኘ ፡ ሰው ፤ በረከት ፡ ካገኘ ፡ ሞገስ ፡ ከሆነለት እንዲህ ፡ ላደረገው ፡ ምሥጋና ፡ ይብዛለት እንዲህ ፡ ላደረገው ፡ ጭብጨባ ፡ ይብዛለት ይህን ፡ ላደረገው ፡ እስኪ ፡ ተቀኙለት ይህን ፡ ላደረገው ፡ ዕልልታ ፡ ይብዛለት ከምሥጋና ፡ ሌላ ፡ የሚሰጠው ፡ የለም ከዕልልታ ፡ ሌላ ፡ የሚሰጠው ፡ የለም ከጭብጨባ ፡ ሌላ ፡ የሚሰጠው ፡ የለም ከዝማሬ ፡ ሌላ ፡ የሚሰጠው ፡ የለም እንዲህ ፡ ላደረገው ፡ ምሥጋና ፡ ይብዛለት እንዲህ ፡ ላደረገው ፡ ጭብጨባ ፡ ይብዛለት ይህን ፡ ላደረገው ፡ እስኪ ፡ ተቀኙለት ይህን ፡ ላደረገው ፡ ዕልልታ ፡ ይብዛለት ከምሥጋና ፡ ሌላ ፡ የሚሰጠው ፡ የለም