Loading
Singer
የሚያውቅልኝ ፡ ጌታ ፡ ያውቅልኛልና ሰው ፡ አልደገፍም ፡ ይሰበራልና ዛሬ ፡ ታይቶ ፡ ነገ ፡ በሚጠፋው ፡ ነገር ልቤን ፡ በዚያ ፡ አልጥልም ፡ አለልኝ ፡ እግዚአብሔር (፪x) አለልኝ ፡ እግዚአብሔር (፬x) አለልኝ ፡ አለልኝ ፡ የሚያስብልኝ (፪x) የበላይ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ የሁሉ ፡ በላይ እኩያ ፡ የሌለህ ፡ በምድር ፡ በሰማይ (፪x) አምላክ ፡ አለኝና ፡ ሁሉን ፡ በእጁ ፡ የያዘ ሥሙም ፡ ድንቅ ፡ መካር ፡ ኃያል ፡ የተባለ ሰማይና ፡ ምድርን ፡ በቃሉ ፡ እንዳፀና እርሱን ፡ ባይሁ ፡ ጊዜ ፡ እኔም ፡ ልቤ ፡ ፀና (፭x) ግራ ፡ አይገባኝም ፡ ነገን ፡ አስቤ ፡ ለወደፊቱ የታመንኩበት ፡ ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ነው ፡ ሁሉ ፡ በደጁ የእንቆቅልሽ ፡ ሁሉ ፡ መፍቻ ፡ ቁልፍ ፡ ያለው የይሁዳ ፡ አንበሳ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ነው እንዳለው ፡ ነው ፡ እንደ ፡ ቃሉ ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ሁሉ ፡ በደጁ እንዳለው ፡ ነው ፡ (እንዳለው ፡ ነው) እንደ ፡ ቃሉ ፡ (እንደ ፡ ቃሉ) ሁሉ ፡ በእጁ ፡ (ሁሉ ፡ በእጁ) ሁሉ ፡ በደጁ ፡ (ሁሉ ፡ በደጁ) (፪x) የበላይ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ የሁሉ ፡ በላይ እኩያ ፡ የሌለህ ፡ በምድር ፡ በሰማይ (፪x)