Loading
Singer
የሚያስፈልገኝን ፡ እርሱ ፡ ያውቃል የሰማይ ፡ አባቴ ፡ ለኔ ፡ ያስባል እጆቼን ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ ዘረጋለሁ በዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ እታመናለሁ የሚያስጨንቀን ፡ በእርሱ ፡ ጥዬ እታመናለሁኝ ፡ በጌታዬ ጽድቁና ፡ መንግሥቱን ፡ እሻለሁኝ ክብሩን ፡ እያየሁኝ ፡ እጠግባለሁኝ ላመልከው ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ የፈጠረኝ ከእርሱ ፡ ሌላ ፡ ምንም ፡ ላይገዛኝ እያሞጋገስኩኝ ፡ ታላቅ ፡ ስሙን አመልከዋለሁኝ ፡ እግዚአብሔርን የጠራኝ ፡ የለየኝ ፡ የቀደሰኝ ለእርሱ ፡ ካህን ፡ ልሆን ፡ ነው ፡ የቀባኝ እርሱ ፡ ያደረገኝ ፡ እሆናለሁ የኣምላኬን ፡ በጐነት ፡ አወራለሁ መልካሙን ፡ ስራውን ፡ የጀመረው የጠራኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ታማኝ ፡ ነው እስከ ፡ ክርስቶስ ፡ ቀን ፡ ሊፈጽመው ይችላል ፡ አምላኬ ፡ ታማኝ ፡ ነው