Loading
Singer
"ከቶ ፡ አይቸኩልም ፡ ዘግይቶ ፡ ይነሳል ግን ፡ ማንም ፡ አይቀድመው ፡ ፈጥኖ ፡ ይደርሳል በምድረ ፡ በዳ ፡ ምንጭ ፡ የሚያፈልቀው ይሄ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ የምናመልከው አንተ ፡ የምትተኛ ፡ ንቃ ፡ ተነሳ ክርስቶስ ፡ ከላይ ፡ ያበራልሃል ሃይል ፡ ለሌለው ፡ ሃይል ፡ ይጨምራል የደከመው ፡ መደገፍያ" አዝ:- ለደከመው ፡ ህይልን ፡ ያስታጥቃል የሞተውን ፡ በሕይወት ፡ ያኖራል ለስልጣኑ ፡ ማነው ፡ ያልተረታ ዛሬም ፡ ነገም ፡ የሚያኮራ ፡ ጌታ (፪x) የሚያኮራ ፡ ጌታ ፡ የሚያኮራ (፬x) የሚያስመካ ፡ ጌታ ፡ የሚያስመካ (፬x) በእሳቱ ፡ ውስጥ ፡ አለፍኩ ፡ አላቃጠለኝም በወንዙ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ አላሰጠመኝም ምህረቱ ፡ እንደጋሻ ፡ ሆኖ ፡ እየከለለኝ ጠላቴ ፡ ሞቷል ፡ ሲል ፡ በሕይወት ፡ አለሁኝ አዲሱን ፡ ዝማሬ ፡ ይዤ ፡ ወጥችሃለሁ የጠላቴን ፡ መንደር ፡ አሸብረዋለሁ አምላኬ ፡ እንደንስር ፡ ሃይሌን ፡ አድሶታል ስሙን ፡ እየጠራሁ ፡ ቀንበር ፡ ይሰበራል አዝ:- ለደከመው ፡ ህይልን ፡ ያስታጥቃል የሞተውን ፡ በሕይወት ፡ ያኖራል ለስልጣኑ ፡ ማነው ፡ ያልተረታ ዛሬም ፡ ነገም ፡ የሚያኮራ ፡ ጌታ (፪x) የሚያኮራ ፡ ጌታ ፡ የሚያኮራ (፬x) የሚያስመካ ፡ ጌታ ፡ የሚያስመካ (፬x) ቀይ ፡ ባሕር ፡ ከፊቴ ፡ ቆሞ ፡ ሲያስጨንቀኝ ሰራዊት ፡ እሁአላ ፡ ተግቶ ፡ ሲከተለኝ እጆቼን ፡ አንስቼ ፡ አምላኬን ፡ ጠራሁኝ ሰመጠ ፡ ፈርዖን ፡ በዐይኖቼ ፡ እያየሁኝ በተዐምር ፡ ነው ፡ እኮ ፡ ጌታ ፡ የሚያኖረኝ ስንትን ፡ አሳልፎ ፡ ቅጥሩን ፡ አዘለለኝ ባሕር ፡ ተከፍሎልኝ ፡ በድል ፡ ተሻግሬ አልጠገብኩም ፡ ገና ፡ ለክብሩ ፡ ዘምሬ አዝ:- ለደከመው ፡ ህይልን ፡ ያስታጥቃል የሞተውን ፡ በሕይወት ፡ ያኖራል ለስልጣኑ ፡ ማነው ፡ ያልተረታ ዛሬም ፡ ነገም ፡ የሚያኮራ ፡ ጌታ (፪x) የሚያኮራ ፡ ጌታ ፡ የሚያኮራ (፬x) የሚያስመካ ፡ ጌታ ፡ የሚያስመካ (፬x)