Loading
Singer
ፀሐይ ፡ አሽቆልቁላ ፡ በምዕራብ ፡ ስትጠልቅ ለምሽት ፡ ተረኛ ፡ ለጨረቃ ፡ ስትለቅ ጐኔን ፡ ላሳርፈው ፡ ከቀኑ ፡ ድካሜ ስተኛ ፡ እንቅልፌ ፡ ሲያደርሰኝ ፡ በህልሜ ህልሜ ፡ ቅዥእት ፡ ሆኖ ፡ ጨለማው ፡ በርትቶ እጥፍ ፡ ሲሆን ፡ ሌቱ ፡ ሲረዝም ፡ ምሽቱ አቤቱ ፡ ወደአንተ ፡ ድምጼን ፡ አሰማለሁ ፈጥነህ ፡ እንደትመጣ ፡ እለምንሃለሁ አዝ፦ የሚረዳኝ ፡ የለምና ፡ ከጐኔ ፡ አትራቅ የሚያግዘኝ ፡ የለምና ፡ ከጐኔ ፡ አትራቅ ፀጥ ፡ ረጭ ፡ ባለው ፡ ሰዓት ኮቴ ፡ በሌለበት ፡ ሁሉ ፡ ቤቱ ፡ ከቶት ፡ እፎይ ፡ በሚልበት ሃሳቤን ፡ ሚጋራ ፡ ጆሮ ፡ የሚሰጠኝ ሲጠፋ ፡ ከጐኔ ፡ ጭንቄን ፡ ሚካፈለኝ የሕይወቴ ፡ ብርሃን ፡ በጽልመት ፡ ሲሞላ የልቤ ፡ ትርታ ፡ በሃይል ፡ ሲመታ አቤቱ ፡ ወደአንተ ፡ ድምጼን ፡ አሰማለሁ ፈጥነህ ፡ እንድትመጣ ፡ እለምንሃለሁ አዝ፦ የሚረዳኝ ፡ የለምና ፡ ከጐኔ ፡ አትራቅ የሚያግዘኝ ፡ የለምና ፡ ከጐኔ ፡ አትራቅ ድንጋይ ፡ ተንተርሶ ፡ ያንቀላፋው ፡ ያዕቆብ መልካም ፡ ራዕይ ፡ አይቶ ፡ ተስፋው ፡ ሲያብብ የቀድሞው ፡ ታሪኩን ፡ ሥሙን ፡ ለውጠኀው የብዙዎች ፡ አባት ፡ እስራኤል ፡ ነህ ፡ አልከው ጭኑ ፡ የተነካ ፡ እግሩ ፡ የሚያነክስ ሁለት ፡ ሰራዊት ፡ ነው ፡ ነግቶለት ፡ ሲመለስ ልታድነኝ ፡ ብትወድ ፡ ፈጥነህ ፡ ጐህ ፡ ሳይቀድ ሊነጋ ፡ አያቅላላ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ሳትመጣ አዝ፦ የሚረዳኝ ፡ የለምና ፡ ከጐኔ ፡ አትራቅ (ከጐኔ) የሚያግዘኝ ፡ የለምና ፡ ከጐኔ ፡ አትራቅ (፪x) አትራቅ