Loading
Singer
የሚመስልህ ፡ የለም ፡ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ ፡ የሚመስልህ ፡ የለም ፡ አንተ ፡ ድንቅ ፡ ነህ የሚመስልህ ፡ የለም ፡ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ የሚመስልህ ፡ የለም ፡ አንተ ፡ ልዩ ፡ ነህ ምህረትህ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ከሕይወት ፡ ይሻላል ፍቅርህም ፡ ጥልቅ ፡ ነው ፡ እንደሞት ፡ ይበረታል ትዕግሥትህ ፡ ታላቅ ፡ ነው ፡ ዘመናት ፡ ያልፋል እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነህ ፡ ማን ፡ ይመስልሃል በዘለዓለም ፡ ዙፋን ፡ በክብር ፡ ተቀምጠሃል እግዚአብሔር ፡ ብርሃን ፡ ነህ ፡ ብርሃንን ፡ ለበሰሃል በቃልህ ፡ ሰማይን ፡ ምድር ፡ ፈጥረሃል ኤልሻዳይ ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ ሁሉ ፡ ይቻልሃል ሁሉን ፡ ታደርግ ፡ ዘንድ ፡ ቻይ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ምድርና ፡ ሞላዋን ፡ ተመለከታለህ ከቅዱስ ፡ ማደሪያ ፡ ትህዛዝ ፡ ትሰጣለህ ፍጥረትን ፡ በሙሉ ፡ አንተ ፡ ትገዛላህ ሰማይት ፡ ክብርህን ፡ ይናገራሉ ፍጥረታት ፡ በሙሉ ፡ ድምጽህን ፡ ይሰማሉ ፡ ለቃልህ ፡ በፍርሃት ፡ ይታዘዛሉ ክብርን ፡ በሙሉ ፡ ለአንተ ፡ ያመጣሉ እግዚአብሔር ፡ አንተ ፡ የለም ፡ የሚመስልህ እጅግ ፡ ከፍ ፡ ያልክ ፡ ነህ ፡ በግርማ ፡ ሞገስህ ሰው ፡ በኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ አንተን ፡ ይቀርብሃል በእውነት ፡ በመንፈስ ፡ ደግሞ ፡ ይሰግድልሃል