Loading
Singer
Updated 1d ago
ሥራችንን ፡ ለእሳት ፡ መቃጠል ፡ አሳልፈን ፡ ብንሰጥም በመልአክት ፡ ልሳን ፡ እንኳን ፡ ብንናገርም ተራሮችን ፡ እስከናፈርስ ፡ እምነት ፡ ቢኖረንም ፍቅር ፡ ግን ፡ ከሌለን ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ አይጠቅምም አዝ፦ ከሁሉ ፡ የሚበልጠዉ ፡ መንገድ ፡ መንገድ ፍቅር ፡ ነውና ፡ በእርሱ : እንሂድ (፪x) አንዲያ ፡ ልጁን ፡ እስኪሰጠን ፡ ድረስ ፡ ከወደደን በደላችንን ፡ ሳይቆጥር ፡ ከእራሱ ፡ ጋር ፡ ካስታረቀን ከወንድማማች ፡ መዋደድ ፡ ነፍሳችንንም ፡ አጥተን እንጓዝ ፡ ከሁሉ ፡ በሚበልጠው ፡ መንገድ ፡ እያስተዋልን አዝ፦ ከሁሉ ፡ የሚበልጠዉ ፡ መንገድ ፡ መንገድ ፍቅር ፡ ነውና ፡ በእርሱ ፡ እንሂድ ፡ (፪x) በፍቅር ፡ የሚኖር ፡ በእግዚአብሔር ፡ ይኖራል በእግዚአብሔርም ፡ በእርሱ ፡ ኑሮና ፡ ህይወት ፡ ይታያል ጌታ ፡ ለእርሱ ፡ ያለውን ፡ ፍቅር ፡ ያወቀ ፡ ቢኖር ባለ ፡ እንጀራውን ፡ እንደራሱ ፡ ይውደድ ፡ በደልን ፡ አይቁጠር አዝ፦ ከሁሉ ፡ የሚበልጠዉ ፡ መንገድ ፡ መንገድ ፍቅር ፡ ነውና ፡ በእርሱ ፡ እንሂድ ፡ (፪x) ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ ማለትን ፡ መተጣጠብ ፡ ሲኖር በፍቅር ፡ አንዱ ፡ ለሌላው ፡ እራሱን ፡ ማስገዛት ፡ ሲጀምር አቤት ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቤት ፡ ውበቱ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ መዓዛው ፍቅር ፡ ነውና ፡ የርስቱ ፡ ዋና ፡ መለያው አዝ፦ ከሁሉ ፡ የሚበልጠዉ ፡ መንገድ ፡ መንገድ ፍቅር ፡ ነውና ፡ በእርሱ ፡ እንሂድ ፡ (፪x) ባለእንጀራችንን ፡ እንደ ፡ እራሳችን ፡ እንውደድ ድካሙን ፡ እያየን ፡ በድፍረት ፡ አንፍረድ እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነውና ፡ በፍቅር ፡ እንኑር ይሄ ፡ ነው ፡ መታወቂያው ፡ የጌታ ፡ ደቀመዝሙር አዝ፦ ከሁሉ ፡ የሚበልጠዉ ፡ መንገድ ፡ መንገድ ፍቅር ፡ ነውና ፡ በእርሱ ፡ እንሂድ ፡ (፪x) ለእግዚአብሔር ፡ ያለን ፡ ፍቅር ፡ የሚረጋገጠው በአጠገባችን ፡ ያለውን ፡ ወንድማችንን ፡ ስንወደው ፡ ነው ጌታ ፡ ደስ ፡ በሎት ፡ መስዕዋታችንን ፡ የሚያሸተው በደልን ፡ ይቅር ፡ የሚል ፡ ጥሩ ፡ ልብ ፡ ሲኖረን ፡ ነው አዝ፦ ከሁሉ ፡ የሚበልጠዉ ፡ መንገድ ፡ መንገድ ፍቅር ፡ ነውና ፡ በእርሱ ፡ እንሂድ ፡ (፪x)